የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
የሴቶች ኮሚሽን
ተግባርና ኃላፊነት

ኮሚሽኑ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሚያዚያ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባሳለፈው ውሣኔ መሠረት የተቋቋመ ነው፡፡

የተቋቋመበት አላማ

 • በሴቶችና ስፖርት ጉዳዮች የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ቦርድን በአማካሪነት ለማገልገል፣
 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሴቶች የስፖርት ተሳትፎን የሚመለከቱ ስራዎችን ኃላፊነት ወስዶ በማከናወን ለቦርዱ ውሣኔ ግብዓት ለማቅረብ፣

የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት

 • በሴቶችና ስፖርት ጉዳዮች የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ቦርድን በአማካሪነት ለማገልገል፣
 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሴቶች የስፖርት ተሳትፎን የሚመለከቱ ስራዎችን ኃላፊነት ወስዶ በማከናወን ለቦርዱ ውሣኔ ግብዓት ለማቅረብ፣
 • የሀገሪቱ ሴቶች የስፖርት ተሳትፎ (በስፖርተኝነት፣ በባለሙያነት፣ በአስተዳዳሪነት፣ ወዘተ…) የሚያድግበትን ስልት ይነድፋል፣
 • በሀገሪቱ ስፖርት ውስጥ ተሣትፎ ያላቸውን ሴቶችን የማበረታቻና የማትጊያ ስልቶችን ይነድፋል፣ ሲፀድቅለትም ይተገብራል፣
 • በሴቶች ስፖርት ላይ ከሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር የልምድ መለዋወጫ፣ የጋራ መርሃ-ግብር መንደፊያ፣ ወዘተ  መድረኮችን ያመቻቻል፣
 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የረዥምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ የሴቶች ተጠቃሚነትን ያገናዘበ እንዲሆን ያማክራል፣ አብሮ ይሰራል፣
 • ከሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ የሚመሩለትን ሥራዎች ያከናውናል፣
 • በሴቶችና ስፖርት ጉዳይ ለፕሬዚዳንቱና ለሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ በአማካሪ ቦርድነት ያገለግላል፡፡
 • ዓመታዊ የሥራ ዕቅዱን አዘጋጅቶ በሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ ያፀድቃል
 • በየሩብ ዓመቱ ስለኮሚሽኑ የሥራ አፈፃፀም የሥራ ሪፖርት ለሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያቀርባል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result