የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
የቴክኒክ ኮሚሽን
ተግባርና ኃላፊነት

ኮሚሽኑ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሚያዚያ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባሳለፈው ውሣኔ መሠረት የተቋቋመ ነው፡፡

 

የተቋቋመበት አላማ

 • በቴክኒካዊ ጉዳዮች የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ቦርድን በአማካሪነት ለማገልገል፣
 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቴክኒካዊ ስራዎችን ኃላፊነት ወስዶ ለማከናወን ለቦርዱ ውሣኔ ግብዓት ለማቅረብ፣

የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት

 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከልዩ ልዩ ሃገራትና ማህበራት የሚያገኛቸው የአጭርና የረዥም ጊዜ የስፖርት ሙያ ስልጠናዎች ተሳታፊዎችን ይመርጣል፡፡
 • ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት አስተዎፅኦ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች፣ አውደጥናቶች፣ ምርምሮችና ጥናቶች ዕቅድና የሚካሄዱበትን ስልትና መርሃ-ግብር ያቀርባል፣ ሲፀድቅለትም ከሚመለከታቸው ጋር ተቀናጅቶ ይተግብራል፣
 • የአራት ዓመት የስልጠና ፍላጎትና አቅርቦት ጥምረትን ያጠናል፣ በአቅርቦት የሚታዩ ማነሶችን የማካካሻ ዘዴ እና የማስፈፀሚያ ስልት ያቀርባል፣
 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጂምናዚየም አገልግሎት ውጤታማ አሰራር እንዲኖረው ስልት ይነድፋል፣ ክትትል ያደርጋል፣
 • ለፕሬዚዳንቱና ለሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በቴክኒካዊ ጉዳዮች በአማካሪ ቦርድነት ያገለግላል፣
 • ከሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ የሚመሩለትን ተዛማጅ ሥራዎች ይሰራል፡፡
 • ዓመታዊ የሥራ ዕቅዱን አዘጋጅቶ በሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ ያፀድቃል
 • በየሩብ ዓመቱ ስለኮሚሽኑ የሥራ አፈፃፀም የሥራ ሪፖርት ለሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያቀርባል፡፡
 • የመላው ኢትዮጲያ ጨዋታ፣ የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ፣ የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ፣ የመላው አፍሪካ ጨዋታ እና የኦሊምፒክ ጌምስ ጨዋታዎችን ዝግጅቶች ተሳትፎ ይከታተላል ይደግፋል ይቆጣጠራል ይገመግማል፡፡
 • ለኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዝግጅት ከሚቋቋመው ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን እስትራቴጂክ እቅዶችን ያወጣል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result