የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
የህክምና ኮሚሽን
ተግባርና ኃላፊነት

ኮሚሽኑ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሚያዚያ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባሳለፈው ውሣኔ መሠረት የተቋቋመ ነው፡፡

የተቋቋመበት አላማ

 • በኦሊምፒክ ፍልስፍናዎች በመመራት የስፖርት እንቅስቃሴን በዘመናዊ ሳይንሳዊ የሕክምና ዘዴ አማካኝነት በመደገፍና በመከታተል ስፖርት ከፍተኛ እድገትን እንዲያስመዘግብና ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል፡፡
 • የአትሌቶችን ሁለንተናዊ ጤንነት መጠበቅ፣
 • የስፖርትን ብሎም የስፖርት ሕክምናን የሙያ ህግጋት መብቶች ማስጠበቅ፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት

 • በስፖርት ሕክምና መስክ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ማማከርና መደገፍ፡፡
 • ስለስፖርቱ ሂደት በምርምር ረገድ የሚገኙትን አዳዲስ ግኝቶች በማሰባሰብ በሥራ ላይ ማዋል፣ ሌሎች አገራዊ ጥናቶችንም ማካሄድ፡፡
 • ለስፖርተኞች የሚያገለግሉ የተለያዩ የስፖርት ሕክምና ነክ የሆኑ መመሪያዎችን ማዘጋጀት
 • ባጠቃላይ በስፖርት ስለስፖርት ዓላማዎች፣ ስለስልጠናና ስለአመጋገብ፣ የብቃት መለኪያ፣ እሽታ፣ ጐጂ ልማዶች፣ ዶፒንግና የመሳሰሉት ዓመታዊ እቅድ፣ በጀትና የድርጊት መርሃ ግብር ይነድፋል፡፡
 • ከኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሚወጣው ሥርዓተ ተግባር ፕሮግራም መሠረት በብሄራዊ ፌዴሬሽኖች የሚገኙ አሰልጣኞችን /ስፖርተኞችን/ ዳኞችን በስፖርት ሕክምና ዘርፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናሮች ወርክሾፕና / ሲምፖዚየሞች ያዘጋጃል፡፡
 • የፀረ ዶፒንግ ሀገራዊ ትግል በተጠናከረና በተባበረ ሁለንተናዊ አቅም ከብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውና ከአህጉራዊ አለም አቀፋዊ ፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲዎች ጋር በመሆን ያከናወናል፡፡
 • በአለም አቀፍ ኮሚሽን ሀገራችን ልትጠቀምበት የምትችለውን የስፖርት ሕክምና ነክ ድጋፍ ፕሮጀክቶችንና ጥናቶችን በማከናወን በሥራ አስኪያጅ ኮሚሽን ለማፅደቅ ይልካል/ ድጋፍም እንደተገኘ በእቅድ በመመራት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
 • በፀረ ዶፒንግ ትግል በጀግኖች የኦሊምፒክ አትሌቶች ፖስተሮችን በተለያዩ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ቋንቋዎች በማዘጋጀት ያሰራጫል፡፡
 • ኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስር የስፖርት ሕክምና አጠቃላይ ክብካቤን በማጠናከር የስፖርት የጤና ማዕከል የሚደራጅበትን ጥናት ያጠናል በተግባር እንዲውልም ለዋናው ኮሚሽን ያቀርባል፡፡
 • ከአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ለሚሳተፍባቸው ውድድሮች የስፖርት ሕክምና መመሪያና የሕክምና መድሃኒቶችን ቅመሞች በጀት ያስመድባል፡፡
 • በየሩብ ዓመቱ ስለኮሚሽኑ የሥራ አፈፃፀም የሥራ ሪፖርት ለሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያቀርባል፡፡
Total votes : 9
Return to Poll