የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
የልማት ኮሚሽን
ተግባርና ኃላፊነት

ኮሚቴው የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሚያዚያ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባሳለፈው ውሣኔ መሠረት የተቋቋመ ነው፡፡

የተቋቋመበት አላማ

  • የግንባታ ጉዳዮች በተመለከተ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድን በአማካሪነት ለማገልገል፡፡
  • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የግንባታ ስራዎችን ኃላፊነት ወስዶ ለማከናወን ለቦርዱ ውሳኔ ግብዓት ለማቅረብ፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • በኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኃላፊነት ስር ለሚከናወኑት የኦሊምፒክ ማዕከል፣ የኦሊምፒአፍሪካ ቢሾፍቱ የወጣቶች ማዕከል ግንባታ እና እምቧይ መስክ መዝናኛ ማዕከልን በተመለከተ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ የማማከርና ስራዎችን የመከታተል፣
  • የግንባታ ስራዎች ተጀምሮ የተጓተቱና ያልተጀመሩበትን ችግር አጥንቶ የመፍትሄ ሃሳብ ለቦርድ ያቀርባል፣
  • የግንባታ ስራዎች ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግብአቶች የሚገኙበትን ስልትና መርሀግብር ማቅረብ፣ ተቀባይነትም ሲያገኙ ተግባራዊነቱን መከታተል፡፡
  • የግንባታ ስራዎች አስጀምሮ ለማስጨረስ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ይቀይሳል፣ በቦርዱ ሲተመንበት ተግባራቸውን ይከታተላል፣
  • ለፕሬዚዳንቱና ለሥራ አስፈፃሚው ቦርድ የግንባታ ጉዳዮች በተመለከተ በአማካሪነት ያገለግላል፡፡
  • ከሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ የሚመሩለትን ተዛማጅ ስራዎች ይሰራል፡፡
  • ዓመታዊ የስራ ዕቅዱን አዘጋጅቶ በሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ ያፀድቃል፡፡
  • በየሩብ ዓመቱ ስለኮሚቴው የሥራ አፈፃፀም የስራ ሪፖርት ለሥራ አስፈፃሚ ቦርዱ ያቀርባል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result