የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ
የአትሌት ኮሚሽን
ተግባርና ኃላፊነት

ኮሚሽኑ የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሚያዚያ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባሳለፈው ውሣኔ መሠረት ነው የተቋቋመው፡፡

የተቋቋመበት አላማ

 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በበጋና በክረምት የኦሊምፒክ ውድድሮች ተካፋይ የሆኑ አትሌቶችን በተመለከተ ማማከር፡፡
 • የኢትዮጲያ አትሌት መብትና ፍላጎት እንዲከበር ማድረግ፡፡
 • የኢትዮጲያ አትሌት በየደረጃው እንዲደራጁ ማድረግ፡፡
 • ከኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌትስ ኮሚሽን እና በስሩ ካሉ አካላት ጋር ግንኙነት መፍጠር፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ዋና ተግባራት

 • የኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ኢንተርናሽናል አትሌት ኮሚሽን እና በስሩ የሚገኙ አካላት የሚያወጧቸውን ሕጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
 • በየስፖርቱ አይነት የአትሌት ኮሚሽን እንዲደራጅ ተገቢው ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 • በየስፖርቱ ያሉ አትሌት ኮሚሽኖችን ይመዘግባል፡፡
 • ከሚመለከታቸው አባላት ጋር በመተባበር አትሌትን የሚመለከቱ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ያዘጋጃል፡፡
 • አትሌትን በተመለከተ ልዩ ልዩ መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፡፡
 • አትሌትን የስፖርትን ሕጎችን ደንቦች እንዲያውቁትና እንዲያከብሩ እንዲሁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲያጎለብቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ዘርግቶ ይተገብራል፡፡
 • አትሌት ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅድ ይነድፋል ይተገብራል፡፡
 • አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለኢትዮጲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያቀርባል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result