የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እ.ኤ.አ በ1948 ተጠንስሶ እ.ኤ.አ በ1954 በአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሜቴ እውቅና ተሰጠው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ድንብ (ቻርተር) መሠረት በስፖርት ፌዴሬሽኖችና ማህበራት ጥንቅር የተቋቋመ ኮሚቴ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ከሚቴ የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን በማስፋፋትና በመጠበቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች አንድትሳተፍ በማድርግ የሀገሪቷን ገጽታ በመገንባት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ተልዕኮ አንግቦ እየሰራ ይገኛል፡፡ በ2017 ዓ.ም የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገና በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተሳታፊና ውጤታማ የሆነ ዜጋ ተፈጥሮ ማየትን እንደ ርዕይ ሠንቆ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ኮሚቴው የኢትዮጵያ አትሌቶች በአህጉርና አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን የገንዘብ፣ የቴክኒክ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡


የኦሊምፒክ ጨዋታዎች

በአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የበላይ አመራርና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በአራት ዓመት አንድጊዜ የሚዘጋጅ፣ ሀገራችን በበርካታ የስፖርት ዓይነቶች እንድትወዳደርና በአለም መድረክ አመርቂ ድሎች እንዲመዘገቡ፣ የሀገራችን ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብና የሀገራችን መልካም ገጽታ እንዲገነባ በዋናነት በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚከወን ጉልህ ስራ ነው፡፡ ኮሚቴው የኦሊምፒክ ዋንኛ ምሶሶ የሆኑትን የኦሊምፒክ ፕሮግራሞች ስትራቴጂክ እቅዱን መሠረት አድርጎ እየተገበረ ይገኛል፡፡ ፕሮግራሞቹ የኦሊምፒክ እሴቶች እና መርሆችን ማዕከል አድርገው የኢሊምፒክ እንቅስቃሴን እና ኦሊምፒዝምን ለማስፋፈት ያለሙ ናቸው፡፡

 

ተልዕኮ

የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ በማስፋፋትና በመጠበቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራችን ተሳትፎ ማሳደግ እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡

ራዕይ

በ2017 የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገና በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተሳታፊና ውጤታማ የሆነ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት፡፡

እሴቶች

•    አሳታፊነት መለያችን ነው፡፡
•    በአካል በአእምሮና በመንፈስ ጠንካራ ጤናማ ዜጋ እንፈጥራለን፡፡
•    በሕዝቦች መካከል ወዳጅነትን እናስፋፋለን፡፡
•    አንዱ ለሌላው ክብር መስጠትን እንሰብካለን፡፡
•    ለተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ እንተጋለን፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዓላማ

ስፖርትን ለሰዎች ጠቀሜታ በማዋል በሰዎች መካከል መግባበትን፣ ወንድማማችነትን መፍጠር፣ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ታንፆ እንዲያድግ በማስተማር ሰላማዊና ቀጣይነት ያለውን ህብረተሰብ መገንባት ነው፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result