አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ እና ካሜሮናዊው ካልካባ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚዳንት ለመሆን ተፋጠዋል

የ76 ዓመቱ አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር የወቅቱ ፕሬዚዳንት ከ 66 ዓመቱ ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል፡፡ 

17ኛው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ከሚቴዎች ማህበር (አኖካ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በጅቡቲ ከግንቦት 1 እስከ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የፕሬዚዳንትነት እና የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫን ዋንኛ አጀንዳው ባደረገው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ይታደማሉ፡፡

የአፍሪካ 54ቱም ሀገሮች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ለፕሬዚዳንትነት ከቀረቡት ሁለት እጩዎች መካከል ለአፍሪካ ኦሊምፒክ እንቅስቃሴ እና ለአህጉሪቷ የስፖርት ዕድገት በጽናት በመቆም ይሰራልናል የሚሉትን መሪያቸውን ይመርጣሉ፡፡

  • 30 April 2017

የቮሊቦል የሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

ከሀገሪቱ ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 30 የቮሊቦል አሠልጣኞች ለአምስት ቀናት የተሰጣቸውን የቮሊቦል ሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ስልጠና ተከታትለው አጠናቀቁ፡፡

ሥልጠናው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከኢንተርናሽናል ቮሊቦል ፌደሬሽን እና ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ጋር በጋራ ተዘጋጅቶ የተሰጠ ነው፡፡

 

 

በሥልጠናው የመዝጊያሥነ-ስርዓት ላይ በአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ የተፈረመ ሠርተፍኬት ለሠልጣኞቹ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ በአቶ ታምራት በቀለ ተሰጥቷቸዋል፡፡

 

  • 28 April 2017


አዲሱ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በስፖርት ልማት ላይ መከረ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የመጀመሪያውን የስራ ጉብኝት የኮሚቴውን የአመራርነት ኃለፊነት ከተረከበ በኋላ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚያዚያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም አካሄደ፡፡

የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ሚያዚያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም መቀሌ ሲገባ በክልሉ አመራሮች በአሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “የስራ ጉብኝቱ አላማ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ጨዋታዎች የሚተርፈው ትሩፋቶች ፋይዳቸው ከፍተኛ መሆን እንዲችሉ ከወዲሁ የቤት ስራችንን በሚገባ ለመስራት ነው፡፡”

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result