የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትን ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፡፡

 


ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የበላይ ጠባቂ ሆነው ይሠራሉ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጽ/ቤታቸው አነጋገሩ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ስፖርታችንን እና የሀገራችን መልካም ገጽታ ግንባታ እንዴት በጋራ እናሳድግ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚኒስቴር መ/ቤቱ መከሩ፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በውይይቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሀገራችን ስፖርት እድገት እየበረከተ ያላውን ድጋፍ አመስግነው የዚህን የጋራ ምክክር መድረክ አላማ ሲገልጹ
“በአራት ዓመት የኦሊምፒክ ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ ሀገራችን ለምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጅትና ተሳታፎ ብሎም ውጤታማነት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጋር ተቀናጅቶ መስረት የማይተካ ሚና ነው ያለው”

ፕሬስ ሪሊዝ

እንደደረሠ ጥቅም ላይ የሚውል

የአትሌት መሠረት ደፋር የቤጂንግ አሊምፒክ ሜዳሊያ ወደ ብር አደገ

የአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጻፈው ደብዳቤ ሀገራችን ከተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ “ኢቨንቶች” መካከል በሴቶች የ5 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት መሠረት ደፋር በወቅቱ ያገኘችው የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር ሜዳሊያ ማደጉን አስታወቀ፡፡

በቤጂንጉ 29ኛው ኦሊምፒያድ የአትሌት መሠረት ደፋር ውጤት የተሻሻለው በወቅቱ ቱርኳዊቷ ሯጭ ኤልቫን አብይ ለገሰ የተከለከለ ንጥረ ነገር (ያልተፈቀደ አበረታች ንጥረ ነገር) ተጠቅማ በመገኘቷ ነው፡፡

በተሻሻለው ውጤት መሠረት በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ወርቅ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የመሠረት ደፋር ብር እና በወቅቱ አራተኛ ደረጃ ይዛ የነበረችው ኬንዊቷ ሲሊቪያ ኬቤት ሶስተኛ ደረጃን ተጓናጽፋ የነሀሰ ሜዳሌያውን ታገኛለች፡፡

አትሌት መሠረት ደፋር በቤጂንግ ኦሊምፒክ የገባችበት ሠዓት 15 ደቂቃ ከ 44.12 ሴኮንዶች ነበር፡፡

“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ከዚህ በፊት የምናውቀው ለገንዘብ ልመና ሲጎበኘን ነው፡፡” አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ርዕሠ መስተዳድር

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በሶስተኛ የስራ ጉብኝቱ ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጋር ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም በመገናኘት ስለ ስፖርት ልማት መከረ፡፡
የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በመጀመሪያ ቀን የስራ ጉብኝቱ ከክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ከአቶ ደሴ ዳልኬ እና ከክልሉ ካቤኔ አባላት ጋር በመስተዳድሩ ቢሮ ስለሀገራችን የስፖርት ልማት መክረዋል፡፡
የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የስራ ጉብኝቱን አላማ አስመልክተው ሲገልጹ
“ሀገራችን በምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማነታችን እንዲረጋገጥ ስራችንን ከወዲሁ በበቂ ዝግጅት መጀመር ስላለብን የስራ ጉብኝቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡”

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result