ፕሬስ ሪሊዝ

እንደደረሠ ጥቅም ላይ የሚውል

የአትሌት መሠረት ደፋር የቤጂንግ አሊምፒክ ሜዳሊያ ወደ ብር አደገ

የአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጻፈው ደብዳቤ ሀገራችን ከተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ “ኢቨንቶች” መካከል በሴቶች የ5 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት መሠረት ደፋር በወቅቱ ያገኘችው የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር ሜዳሊያ ማደጉን አስታወቀ፡፡

በቤጂንጉ 29ኛው ኦሊምፒያድ የአትሌት መሠረት ደፋር ውጤት የተሻሻለው በወቅቱ ቱርኳዊቷ ሯጭ ኤልቫን አብይ ለገሰ የተከለከለ ንጥረ ነገር (ያልተፈቀደ አበረታች ንጥረ ነገር) ተጠቅማ በመገኘቷ ነው፡፡

በተሻሻለው ውጤት መሠረት በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ወርቅ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የመሠረት ደፋር ብር እና በወቅቱ አራተኛ ደረጃ ይዛ የነበረችው ኬንዊቷ ሲሊቪያ ኬቤት ሶስተኛ ደረጃን ተጓናጽፋ የነሀሰ ሜዳሌያውን ታገኛለች፡፡

አትሌት መሠረት ደፋር በቤጂንግ ኦሊምፒክ የገባችበት ሠዓት 15 ደቂቃ ከ 44.12 ሴኮንዶች ነበር፡፡

“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ከዚህ በፊት የምናውቀው ለገንዘብ ልመና ሲጎበኘን ነው፡፡” አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ርዕሠ መስተዳድር

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በሶስተኛ የስራ ጉብኝቱ ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጋር ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም በመገናኘት ስለ ስፖርት ልማት መከረ፡፡
የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በመጀመሪያ ቀን የስራ ጉብኝቱ ከክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ከአቶ ደሴ ዳልኬ እና ከክልሉ ካቤኔ አባላት ጋር በመስተዳድሩ ቢሮ ስለሀገራችን የስፖርት ልማት መክረዋል፡፡
የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የስራ ጉብኝቱን አላማ አስመልክተው ሲገልጹ
“ሀገራችን በምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማነታችን እንዲረጋገጥ ስራችንን ከወዲሁ በበቂ ዝግጅት መጀመር ስላለብን የስራ ጉብኝቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡”የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሁለተኛውን የሥራ ጉብኘት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር አካሄደ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በሁለተኛው የስራ ጉብኝቱ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም በመገኘት ከክልሉ መንግስት ጋር በስፖርት ልማት ዙሪያ መከረ፡፡

የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ.ም የክልሉ መዲና በሆነቸው ባህር ዳር ሲገባ በክልሉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ የባህር ዳር አለም አቀፍ ሁለገብ ስታዲየም እና በባህር ዳር ዩኒቭርስቲ የስፖርት አካዳሚን የስፖርት መሰረተ ልማቶች ጎብኝቷል፡፡

  የኮሚቴው የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት የባህር ዳር ሁለገብ ስቴድየም እና የባህርዳር  ዩኒቨርስቲ ስፖርት አካዳሚ ከጎበኙ በኋላ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጉብኝቱ ክልሉ በስፖርቱ ዘርፍ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ እንዳስቻላቸው ገልፀዋል።


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ለስፖረት ባለሙያዎች እና አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የስፖርት አስተዳደር ኮርስ ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ትብብር ከግንቦት 5-9 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ለአማራ ክልል የስፖርት አመራሮችና ሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው የስፖርት አስተዳደር ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ፡፡


በስልጠናው ላይ 25 ወንዶች እና 10 ሴት ሠልጣኞች በድምሩ 35 ሠልጣኞች ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡
ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ.ም በተካሄደው የስልጠናው የመዝጊያ ስነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ባስተላለፉት መልዕክት
“የወሰዳችሁት የስፖርት አስተዳደር ስልጠና በራሱ የመጨረሻ ግብ አይደለም፡፡”
“ያገኛችሁትን እውቀት፣ ልምድ እና ክህሎት በየደረጃው ለሚመለከታቸው የስፖርቱ ተዋንያን ማካፈል እና ማባዛት ትልቁ የቤት ስራችሁ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
ሠልጣኞቹ ሥልጠናቸውን በስኬት በማጠናቀቃቸው ሠርተፍኬት ተሠጥቷቸዋል፡፡
በስልጠናው የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወጣቶች ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወለላ መብራት  እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ታዳሚዎች ነበሩ፡፡


የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result