ለአምስተኛው መላ የኢትዮጵያ ጨዋታዎች የሶስትዮች ስምምነት ተፈረመ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የአምስተኛውን መላው የኢትዮጵያ ጨዋታዎች በስኬት በሐዋሳ ከተማ ለማካሄድ በአዘጋጁ በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በአስተናጋጁ ክልል የደቡብ ብሔር ብሔረሠቦች ሕዝቦች መካከል ጥቅምት 28 ቀን 2008 ዓ.ም የስምምነት ሠነድ ተፈረመ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሬደዋን ሁሴን በተገኙበት የሶስትዮሽ ስምምነቱ የተፈረመ ሲሆን አዘጋጆች እና አስተናጋጁ ክልል የሚያከናውኗቸው ኃላፊነቶች በዝርዝር በሠነዱ ላይ የተካተተ ሲሆን ዝግጅቱም በአዘጋጁ ክልል ከሞላ ጎደል እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ የሶስትዮሽ ስምምነቱን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ወክለው የተፈራረሙት የኮሜቴው ኤግዚኩዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ “በኦሊምፒክ መርህ የሚከናወነው አምስተኛው መላው የኢትዮጵያ ጨዋታዎች አሸናፊነትና ተሸናፊነት አጀንዳው አይደለም” “ለዘመናት በመከባበር፣ በመቻቻል፣ በፍቅርና በሠላም፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት የመኖር ታሪካችንን ያጠናክርልናል፡፡” ብለዋል፡፡

ስምምነቱ ጨዋታው ስኬታማ እንዲሆን በአስተናጋጅ እና በአዘጋጆች አካላት መካከል ከወዲሁ መከናወን ያለባቸውን ተግባራትን በመለየት ለመፈፀም መሆኑ ታውቋል፡፡ በዘንድሮው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በመጋቢት 2008 ዓ.ም በ18 የስፖርት ዓይነት ከስድስት ሺህ 300 የሚበልጡ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ አንደኛውና ሁለተኛው መላው የኢትዮጵያ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ፣ ሦስተኛው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ አራተኛው ደግሞ በአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት አዘጋጅነት በደመቀ ሁኔታ ተካሂደው ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result