ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች አመርቂ ውጤት አስመዘገበች

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

ለ11ኛ ጊዜ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ ብራዛቪል በተካሄደው የአፍሪካ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በውድድሩ በ11 የስፖርት ዓይነቶች ተሳትፋ 7 የወርቅ፣ 5 የብርና 12 የነሐስ በድምሩ 24 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

11ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር (የአፍሪካ ኦሊምፒክ) የ2016 ሪዮ ዴጄኔሮ ኦሊምፒክ ከመካሄዱ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ መከናወኑ፣ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የልዑክ ቡድን ዝግጅት ከፍተኛ ፉይዳ እና ጠቀሜታ እንዳለው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ኤግዚኩዩቲቭ ዳይሬክተር እና የ2016 ሪዮ ኦሊምፒክ የልዑክ ቡድን መሪ አቶ ታምራት በቀለ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ውድድር የተገኙት ስድስት የወርቅ ሜዳሊያዎች በአትሌቲክስ የተገኙ ሲሆን በወርልድ ቴኳንዶ አንድ ወርቅ ማግኘት ተችሏል።

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result