አቶ ሬድዋን ሁሴን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር እጅና ጓንት ሆነን እንሠራለን አሉ Featured

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ አመራሮች ጋር ሀሙስ ጥቅምት 04 ቀን 2008 ዓ.ም በኮሚቴው ዋና መ/ቤት ስለኮሚቴው የሥራ እንቅስቃሴዎች መከሩ፡፡

ሚኒስትሩን ተቀብለው ያነጋገሩት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም እና የኮሚቴው ኤግዚኩዩቲቭ ዳይይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ ነበሩ፡፡ በምክክር ፕሮግራሙ መጀመሪያ አቶ ታምራት በቀለ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን አደረጃጀት፣ የአሠራር ሥርዓት፣ ኮሚቴው እስካሁን በስራ እንቅስቃሴው ለኢትዮጵያ ስፖርት ዘርፍ በተለይ ለኦሊምፒክ እድገት ያደረገውን አስተዋጽኦ፣ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዝግጅትና አፈጻፀም ዙሪያ ገለጻ ሠጥተዋል፡፡ የኮሚቴው ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሠጥ አጽንኦት ሠጥተው የተናገሩት፣ “ሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ጥቂት ወራት ነው የቀሩት፣ ስለሆነም ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ጎን በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን” ብለዋል፡፡ አቶ ሬደዋን ሁሴን በበኩላቸው የተደረገላቸው ገለጻ እንዳስደሰታቸው እና ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩ፣ የሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዝግጅትና ተሳትፎ አስመልከቶ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በተደራጀ አግባብ ድጋፉን እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

በመጨረሻም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ቤተመጻህፍት እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡ በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካቤኔ አባል ሆነው ከተሾሙት ሚኒስትሮች መካካል በአዲስ መልክ የሚደራጀውን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲመሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result