የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሲሰጥ የቆየዉን በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነዉን የቦክስ ደረጃ ሁለት ኮኮብ የአሰልጣኞች ስልጠና አጠናቀቀ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ እና ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየዉ የቦክስየሁለተኛደረጃኮኮብ የአሠልጣኞችስልጠ፡ና  አጠናቀቀ፡

 

በመዝጊያ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት አቶ ተስፋዬ በቀለ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል እንደተናገሩት በስልጠናዉ ያገኛችሁት የንድፍናየተግባርትምህርትያላችሁንየአሠልጣኝነት ብቃትና ክህሎት በቴክኒክ እና በታክቲክ ከማሳደጉም በተጨማሪ ያገኛችሁትን እውቀት በዘርፉ ላሉ ሞያተኞች በማካፈልና ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት በማፍራት በአህጉር አቀፍና አለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያን የሚያስጠሩ ተተኪዎችን ማፍራት ይጠበቅባችሃል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞቹም በበኩላቸዉ ስልጠናዉ እጅግ በጣም ጠቃሚ ጥሩ እዉቀት ያገኙበት ና የተጣለባቸዉን ሃላፊነት በትጋት እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዉ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክኮሚቴንከተባባሪ አካላቶች ጋር አመስግነዋል፡፡

ስልጠናዉን ሲሰጡ የቆዩት ጋናዊው አለም አቀፍ አሰልጣኝ ሚስተር ኦፎሪ አሳሪከኢትዮጵያ ኦሊምፒክኮሚቴየተበረከተላቸዉን ስጦታ በተቀበሉበት ወቅት እንደተናገሩት በቆይታቸዉ ደስተኛ እንደሆኑና በኢትዮጵያለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠዉ ይህ ስልጠና በአፍሪካ ብዙም የተለመደ እንዳልሆነና ይህንን ስልጠና ማግኘታችሁ እድለኛ  ናችሁ በቀጣይም ጠንክራችሁ በመስራት ስፖርቱን ማሳደግ አለባችሁ  ብለዋል፡፡አሰልጣኙ በበኩላቸዉ የቦክስ አርማን ለኢ. ፍ. ዲ. ሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክኮሚቴ እና ለኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ሰ ጥተዋል 

በመጨረሻም ለሰልጣኞቹ አቶ ተስፋዬ በቀለ  ሰርተፊኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Total votes : 9
Return to Poll