የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነዉን የቦክስ ደረጃ ሁለት ኮኮብ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከጥር 9-15/2010ዓ.ም. ለ7 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቦክስ ደረጃ ሁለት ኮኮብ የአሰልጣኞች ስልጠና ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ እና ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በኢትዮጵያወጣቶችና ስፖርት አካዳሚመስጠት ጀመረ፡፡

 

በኦሊምፒክ መርህና የኢትዮጵያን ስፖርት ፖሊሲን መሰረት በማድረግ ሁሉንም ክልሎች በእኩል የማስተናገድ እና የማብቃት ሀላፊነት ያለበትየኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከ ዘጠኙ የሀገራችን ክልሎችና  ከሁለት ከተማ መስተዳደሮች ይተዉጣጡ 20 የቦክስ ስፖርት አሰልጣኞችና ከኡጋንዳ ሀገር 2 ሰልጣኞች በአጠቃላይ 22 አሰልጣኞች በዚህ ስልጠና ሲሳተፍ  ስልጠናዉ በተግባርና በቲዎሪ ፈተና የተደገፈ ሲሆን ይህንን ስልጠና የሚሰጡት ጋናዊው አለም አቀፍ አሰልጣኝ ሚስተር ኦፎሪ አሳሪ ናቸዉ፡፡

"ይህንን ስልጠናፈተናዉን በማለፍ  ሲያጠናቅቁ በአለም አቀፍ የቦክስ ስልጠና ስታንደርድ መሰረት የደረጃ ሶስት ኮኮብ የአሰልጣኞች ስልጠናበመዉሰድ ኢንስትራክተር የመሆን እድል አላችሁ ይህንንም ከግብ ለማደረስ  ጠንክራችሁ ስሩ በቀጣይም ኮሚቴዉ ከጎናቸዉ ነዉ"ብለዋል የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ ፡፡በተጨማሪም ሀገራችን በቦክስ ስፖርትበ1964 በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተሳተፈችበት ጀምሮ እስከ ቤጂንግ 2008 ኦሊምፒክ ስትሳተፍ ብትቆይም ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን በዚህ ስፖርት በኦሊምፒክ መድረክ መሳተፍ አልቻለችም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም በቶኪዮ 2020 አገራችን ልትሳተፍባቸው እቅድ ከያዘቻቸው 8 ስፖርቶች መካከል ቦክስ አንዱ በመሆኑና  ስፖርቱን ወደ ኦሊምፒክ መድረክ ለመመለስ እና ውጤታማነት ለማጐልበት ይህንን ስልጠና  ተዘጋጅቷዋል ሲሉም አክለዋል፡፡

በመጨረሻም ስልጠናው በይፋ መከፈቱን አብስረዉ ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ያላችሁን ገንቢ ሃሳብ በማከል እና ያላችሁን ልምዶች እርስ በርስ በመለዋወጥ ለክልላችሁ ብሎም ለአገራችን የቦክስ ስፖርት እድገት የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል የኮሚቴዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብርወልደጊዮርጊስ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result