የኢትዮጵያ የስፖርት አመራር ልዑካን ቡድን በደቡብ ኮሪያ የሥራ ጉብኝት አደረጉ ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጋራ በመተባበር የ5ክልል የስፖርት የቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከታህሳስ 22  እስከ  28 ቀን 2010 ዓ.ም. በደቡብ ኮሪያ የስራጉብኝት ደረጉ ነዉ፡፡

 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር በስፖርት ልማት ስራዎች የአመራሩን አቅም ለመገንባት በተለይም የማዘውተሪያ ስፍራዎች አያያዝና አጠቃቀም ላይ ልምድ ለመቀመርና ወደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በመቀየር ለመስራት ብሎም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተደረገ ጉዞ ሲሆን ለዚህ ጉዞ መሳካት በደቡብ ኮሪያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተለይም ክቡር አምባሳደር ሽፈራዉ ጃርሶ ከፈተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡

 

Ø  እንደሚታወቀው ደቡብ ኮሪያ ባሏት የስፖርት መሠረተ ልማቶች ላለፉት በርካታ አስርት አመታት ትልልቅ ስፖርታዊ ውድድሮችን በማስተናገድ አለም አቀፍ ተቀባይነትን ማትረፍ ችላለች፡፡

Ø  እንደኢኮኖሚያዊ ሁሉ በደቡብ ኮሪያ ውስጥ አርአያ የሚሆን የስፖርት እድገት ስላለ:-"ስፖርቱን ማሳደግ ከሚል አስተሳሰብና አሰራር በስፖርቱ ሀገርን ማልማት"ይቻላል ወደ ሚል አሰራር በመምጣታቸው ይህም በሀገሪቱ የስፖርት እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣቱ፣

Ø  በኢትዮጵያ የሚገኘው የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ከስፖርቱ ሴክተር ጋር በቅንጅት በመስራቱና ደቡብ ኮሪያ ሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይህንን ጉዞ በማመቻቸቱ ደቡብ ኮሪያ ለልምድ መቀመሩ ተመራጭ አድርጓታል፡፡

ህ የልዑካን ቡድንን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ የተመራ ሲሆን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሚቴዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና ዋና ፀሀፊዉ አቶ ታምራት በቀለ ከ5 ብሔራዊ ክልሎች የስፖርት ቢሮኃላፊዎች ማለትም:-

1. ከኦሮሚያ አቶ ሞቱማ ተመስገን

2. ከአማራ  ወ/ሮ  ወለላ መብራት

3. ከደቡብ  ወ/ሮ  መሰረት መስቀሌ

4. ከትግራይ አቶ ጐይቶም ይብራህ

5. ከአዲስ አበባ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው    

እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አላዩን ጨምሮ በአጠቃላይ 9 የልዑካን ቡድን አባላት በዚህ ጉዞ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በጉብኝቱ ወቅት ደቡብ ኮሪያ በ1988 ኦሊምፒክን ስታዘጋጅ የገነባችዉን የኦሊምፒክ ፓርክን:በ2002 ደቡብ ኮሪያ ከጃፓን ጋር በመተባበር የአለም የእግር ካስ ዋንጫ ስታዘጋጅ የተገነባዉን ስታዲየም:በ2011 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ያዘጋጀችበት ዴጉ ስታዲየምንና የመሳሰሉት የስፖርት መሰረተ ልማት ጎብኝተዉ ከሚመለከታቸዉ አመራሮች ጋርም የዉይይትና የልምድ ልዉዉጥ ሂደዋል፡፡

ይህ የስራ ጉብኝት በነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ቻይና አገር ከተደረገው የልምድ ልውውጥ ተመሳሳይ እና ቀጣይነት ያለው ሲሆን ይህ የስራ ጉብኝት የሀገራችን የስፖርት ልማት ለማስፋፋት እና ለማገዝ ክልሎችን ለማብቃት እንደሚረዳ ይታመናል፡፡

 

የልምድ ልውውጡ ላይ የሚሳተፉት የክልል አመራሮች ወደ ክልላቸው ተመልሰው ያገኙትን ተሞክሮ በመቀመር በክልላቸው ስፖርትን የማልማት፣ በክልሉ የሚገኙ የማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠቃቀም እና አያያዝ አስፈላጊውን ግንዛቤ ለዘርፉ ተዋንያን የመስጠት፣ የአሰራር ማኑዋል የማዘጋጀት እና ለክልላቸው ብሎም ለሀገር ስፖርት እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

 

 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result