የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየዉ የስፖርት አስተዳደር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያኦሊምፒክኮሚቴ ከወጣቶችናስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከህዳር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት በአዳማ ሲሰጥ የቆየዉ የስፖርት አስተዳደር ስልጠና ትናንት ተጠናቀቀ፡፡ በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉ ከፍተኛ የስፖርት አመራሮችና ባለሞያዎች ቆይታቸዉ ጥሩ እንደነበረና በስልጠናዉ ላይ ያገኙት ዕዉቀት በቀጣይ ላለዉ ስራቸዉ እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ነዉ ቀጣይነት ቢኖረዉ ለስፖረቱ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ሲሉ ነገር ግን የሴቶችን ቁጥር በስፖርት አመራርነት እና ተሳታፊነት ከማሳደግ አንፃር ሚኒስትር መስሪያቤቱም ሆነ የኢትዮጵያኦሊምፒክኮሚቴ ሊያስቡበትና ሊሰሩበት ይገባል በማለት በማጠቃለያ ስነስርዓቱ ላይ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡

 

በዚህ ስልጠና የማጠቃለያ ስነስርዓት ላይ የተገኙትና የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የሆኑት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብርወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው፡-

ያገኛችሁትን እውቀትና ክህሎት በየደረጃው ላሉ አካላት በማድረስ ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት የበኩላችሁን ሚ ና እንደምትወጡ እምነቴ የፀናነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቀጣይም እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችንናበሰፖርት ዉስጥ የሴቶችንየአመራርነት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ እያረጋግጥኩ ስልጠናውን ተከታትላችሁ በማጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡በወጣቶችናስፖርትሚኒስቴር የትምህርትና ስልጠና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰለሞን አላዩ በበኩላቸዉ የስፖርትአመራሩናባለሙያዉ ያገኙትን ዕዉቀትና ልምድ ወክለዉ ለመጡት ክልል ብሎም ለሀገር ስፖርት እድገት እንዲሰሩ ናየከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ስፖርትን ከማህበረሰቡ ጋር በማቆራኘትና በጥናትና ምርምርበመደገፍ እንዲያግዙ የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራትም የሚመሩትን ስፖርት የማስፋፋት ክልሎችን የመደገፍናየመከታተል ሀላፊነት አለባችሁ ብለዋል፡፡

በስተመጨረሻም ስልጠናው ለሰልጣኞች ሰርተፊኬት በመስጠት ተጠናቁዋል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result