የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስፖርት አስተዳደር ስልጠና መስጠት ጀመረ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከህዳር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለ4 ተከታታ ቀናት የሚቆይ የስፖርት አስተዳደር ስልጠና በአዳማ መስጠት ጀመረ፡፡ ይህ ስልጠና ለየት የሚያደርገው በአገር አቀፍ ደረጃ በተለይም ለስፖርት አመራሩና ባለሙያው የተዘጋጀ ሲሆን በስልጠናው ላይ የክልል ስፖርት ዘርፍ አመራሮች፣ የከፍተኛትምህርትተቋማት፣ የሀገርአቀፍስፖርትማህበራት ጽ/ቤትኃላፊዎች፣ የስፖርት ማሠልጠኛ ማዕከላትና እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተሮች በአጠቃላይ ወደ 86 የሚሆኑ የዘርፍ ተዋንያን እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

 

 

በስልጠናው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ እንዳሉት፡-በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የጀመረናቸውን የሰፖርት ል ማት ስራዎችን በላቀ ደረጃ ለመፈፀም፣ቅንጅታዊ ስራዎችን አጠናክረን በጋራ ለመስራትና በስፖርቱ ዙሪያ የሚያጋጥሙትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዕውቀት ላይ ተመስርተን መፍትሔ ለመስጠት ይህ ስልጠና አቅም ይፈጥርልናል ብለዋል፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው፡-

ያለናንተ የዘርፍ ተዋንያን ድጋፍና አጋርነት የኢትዮጵያን ስፖርት ማሳደግ አይታሰብም ስለዚህም ከናንተ ጋር እጅናጓንት ሆኖ በመስራት የሀገራችንን ስፖርት ለማሳደግ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችና ድጋፎችን ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት ልማትንና ኦሊምፒዝምን ብሎም የኦሊምፒክ እሴቶች የሆኑትን ወዳጅነት፣ የላቀ ውጤታማነትን መከባበርን ማዕከል በማድረግ የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እንደዚህ አይነት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት አቅም በፈቀደ አግባብ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

 

ይህም የስፖርት አስተዳደር ስልጠና ያላችሁን የአመራር ብቃትንና ክህሎት እንዲያድግ የራሱ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት እምነቴ የፀና ነው ብለዋል፡፡ ሥልጠናው ሀሙስ ህዳር 21 ይጠቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result