የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጅማ ሲሰጥ የነበረው የስፖርት አስተዳደር ኮርስ ተጠናቀቀ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከህዳር 03 እስከ 07 ቀን 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያ  ክልልበጅማና አካባቢዋ ከሚገኙ 11 ዞኖችና ከተማዎች ለተውጣጡ የስፖርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የስፖርት አስተዳደር ኮርስ ተጠናቀቀ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በስፖርት ውስጥ የስፖርት አመራር ክህሎትን ለማዳበር በ ኦሊምፒክ መርህ  የተቃኘ  አስተሳሰብ ለመፍጠርና ለማስረፅ & ዉጤታማ ስራ ለመስራት ብሎም  ስፖርቱን ለማሳደግ በዕቅድ ላይ የተመረኮዘ  ስልጠና በተለያዩ ክልሎችና ከተማዎች በየደረጃዉ ላሉ የስፖርት አመራሮችና ባለሞያዎች የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና መስጠት ከ ጀመረ ሰንበትበት ያለ ሲሆን ይህ ጅማ እየተሰጠ ያለዉ  የዕቅዱ ዋነኛ አካል ነዉ በዚህ ስልጠና ላይ በጅማና አካባቢዋ ከሚገኙ 11 ዞኖችና ከተማዎች የተውጣጡ የስፖርት አመራሮችና ባለሞያዎች በድምሩ 35 ሰልጣኞችን ያሳተፈ ነዉ ፡፡

በስልጠናው ላይ ከተካፈሉት 35 ሰልጣኞች መካከል 5 ሴት የስፖርት አመራሮች ነበሩ፡፡ ህዳር  7 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደው የስልጠናው የመዝጊያና የሠርተፍኬት አሰጣጥ  ስነ-ሥርዓት ላይ  የተገኙት የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ መሀመድ አባቦር   እንደተናገሩት“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ  የሰጠንን ዕድል ተጠቅማችሁ ያገኛችሁትን እውቀትናልምድ በመቀመር ለስፖርቱ ዕድገት ወደታች ወርዳችሁ የተሻለ እንደምትሰሩ እተማመናለሁ ፡፡”

“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም የሚሰጠንን ስልጠናና ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እናምናለን፡፡”ብለዋል

 ሰልጣኞችም ያገኙትን እውቀት፣ ልምድ እና ክህሎት በየደረጃው ለሚመለከታቸው የስፖርቱ አመራርና ባለሞያዎች የማካፈል ትልቅ የቤት ስራ እንዳለባቸዉ ተናግረዋል በተመሳሳይ ሁኔታ በመቀሌ ከህዳር 1 እስከ 5 ሲሰጥ የነበረዉ የስፖርት አስተዳደር ኮርስ ባለፈዉ ህዳር 5 ለሰልጣኞቹ ሰርተፊኬት በመስጠት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result