የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና በጅማ እየሰጠ ነዉ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከህዳር 03 እስከ 07 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚቆይ የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና በጅማ መስጠት ጀመረ፡፡

ስልጠናዉ በኦሮሚያ ክልል በጅማና አካባቢዋ ከሚገኙ 11 ዞኖችና ከተማዎች የተውጣጡ የስፖርት አመራሮችና ባለሞያዎች በድምሩ 35 ሰልጣኞችን ያካተተ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በስፖርት ውስጥ የስፖርት አመራር ክህሎትን ለማዳበር፡ በ ኦሊምፒክ መርህ የተቃኘ አስተሳሰብ ለመፍጠርና ለማስረፅ ፡ ዉጤታማ ስራ ለመስራትና ብሎም ስፖርቱን ለማሳደግ በዕቅድ ላይ የተመረኮዘ ስልጠና በተለያዩ ክልሎችና ከተማዎች በየደረጃዉ ላሉ የስፖርት አመራሮችና ባለሞያዎች የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና መስጠት ከ ጀመረ ሰንበትበት ያለ ሲሆን ይህ ጅማ እየተሰጠ ያለዉ የዕቅዱ ዋነኛ አካል ነዉይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡ብለዋልየኮሚቴዉ ዋና ፀሀፊ አቶ ታምራት በቀለ

ይህ ስልጠና ሲጠናቀቅ ሰልጣኞች ያገኙትን እዉቀት እና ክህሎት በየደረጃዉ ላሉ አካላት በማድረስ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ያግዛቸዋል፡፡

 

Total votes : 9
Return to Poll