የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና በመቀሌ እየሰጠ ነዉ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበርከህዳር 01 እስከ 05 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚቆይ የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና በመቀሌ መስጠት ጀመረ፡፡ ስልጠናዉ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኙት የ 21 ስፖርት ማህበራት ወይም ፌዴሬሽኖች ፕሬዝዳንቶች የማህበራቱ ፀሀፊዎችና የስፖርት ባለሞያዎች የተውጣጡ በድምሩ 35 ሰልጣኞችን ያካተተ ነዉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የአገሪቱን ስፖርት ከማስፋፋት እና ከማሳደግ አኳያ ከሚሰራቸው በርካታ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካካል ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት አንዱ ነው ያሉት የኮሚቴዉ ዋና ፀሀፊ አቶ ታምራት በቀለ ናቸዉ ፡፡

በተለይም በዘንድሮ አመት የሚካሄደዉን 6ተኛ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የትግራይ ክልል እንደማዘጋጀቱ ይህንንም በተሳካ ሁኔታ ለመምራትና ለመፈፀም ይቻል ዘንድ ኦሊምፒክ ኮሚቴዉ በክልሉ ለሚገኙ ባለሞያዎችና አመራሮች ይህንን የአስተዳደር ስልጠና ለመስጠት ወስኗል ብለዋል፡፡

በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፍ አመራሮችና ባለሞያዎች ክልሉ በሚያዘጋጀዉ 6ተኛዉ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ በተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ላይ በመሳተፍ ያገለግላሉ በቀጣይም ያገኙትን እዉቀት እና ክህሎት በየደረጃዉ ላሉ አካላት በማድረስ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ስፖርት እድገት የበኩላቸዉን እንደሚወጡ ይጠበቃል ሲሉ የኮሚቴዉ ዋና ፀሀፊ አቶ ታምራት በቀለ ተናግረዋል

Total votes : 9
Return to Poll