የኢትዮጰያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የአመራር አባላት ጋር መከረ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

 

የኢትዮጰያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥቅምት 16ቀን 2009ዓ.ም. በኢንተርኮንቴኔንታል አዲስ ሆቴል ከብሔራዊ ፌዴሬሽኖች አመራር አካላት ጋር የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መከረ::

በምክክሩ ወቅት «የኢትዮጰያንስፖርት ማሳደግ ዋናኛ አላማችን ነው;ያሉት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለዚህም አላማ ስኬት ከመንግስትና ከብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ጋር የሶስትዮሽ የጋራ እቅድ አቅደን ተቀራርበን መስራት ከጀመርን ሰንበትበት ብለናል ብለዋል::

 

የኢትዮጰያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የአመራር አባላት ጋር የጋራ መድረክ ሲያዘጋጅ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም የኮሚቴው የስራ አሰፈፃሚ ቦርድ ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል የመጀመሪያውን የጋራ የምክክር መድረክ አካሂደዋል በዚህ በ1ኛው ዙር የምክክር መድረክ ወቅት በየ6ወሩ ለመገናኛትና የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን መገምገም እቅድን መከለስ ስራን ለመከፋፈል በተስማማነው መሰረት ይህንን መድረክ ኮሚቴው በድጋሚ አዘጋጅቷል ብለዋል::

በዚህ የምክክር መድረክ የኮሚቴው ዋና ፀሐፊ አቶ ታምራት በቀለ የኢትዮጰያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያከናወናቸውን ተግባራትና የስፖርት ልማት ስራዎች ሪፖርት 1 ስለ 6ኛው መላ ኢትዮጰያ ጨዋታዎች የተጫዋቾች ተገቢነት ና ቅጣት ጋር በተያያዘ ሰነድ ካቀረቡ በሁዋላ ተሳታፊዎች በቀረቡት ሰነዶቸና ሪፖርት ከድጋፍ አሰጣጥ ሁኔታ ጋር በተያያዘና ተዛማጅ ሀሳቦችን ከሰጡና ከተወያዩ በሁዋላ ለቀጣይ 6 ወራት የሚያከናውኗቸውን የስራ ተግባራት በመከፋፈል ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀዋል::

የአቋም መግለጫውም ከዚህ እንደሚከተለው ነው:-

 

1/ እኛ

የኢትዮጰያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያ እግር ካስ  ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያእጅ ካስፌዴሬሽን

የኢትዮጰያቮሊቮል  ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያቅርጫት ካስፌዴሬሽን

የኢትዮጰያቦክስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያ ውሹ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያኢንተርናሽናል ቴèንዶ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያባህላዊ ስፖርቶች ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያዳርት ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያብስክሌት ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያካራቴ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያጅምናስቲክ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያውሃ ስፖርት ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያባድሜንተን ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያቼዝ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያቦውሊንግ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያየሜዳ ቴኒስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያክብደት ማንሳትና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያኢንተርናሽናል ቴካንዶ  ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያኢንተርናሽናል ፓራሊምፒክ ፌዴሬሽን

የኢትዮጰያሞተር ስፖርት አሶሲዬሽን

የኢትዮጰያፈረስ ስፖርት አሶሲዬሽን

የኢትዮጰያመስማት የተነሳናቸው ስፖርት ፌዴሬሽን

የሀገር አቀፍ የሰፖርት ማህበራት የኢትዮጰያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአጭር ግዜ ውስጥ

የሰራቸው የሰፖርት ልማትና የሀገራችንን የስፖርት  የሚያሳድግ ተግባር በመሆኑ

ተጠናክሮ በዚሁ እንዲቀጥል ተስማመተናል'

2/ የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት በ2010 ዓ.ም. በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

በሚካሄደው  የ6ተኛው  መላው የኢትዮጰያ ጨዋታዎች ላይ የሚሳተፉ ስፖርተኞች

ያለምንም ክልከላ እና ገደብ ሁሉም የሀገራችን ስፖርተኞች ከቅጣት በስተቀር እንዲሳተፉ

ተስማምተናል

3/ እኛ የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት የሀገራችንን የስፖርት እንቅስቃሴዎችን የሚያጨልም

ከኦሊምፒክ መርህ ውጭ የሆኑ የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶችን አጥብቀን እየተቃወምን

ለዚህም ክለቦ የደጋፊ ማህበራት እንዲሁም መላው የሰፖርት ቤተሰብ የፀጥታና

ፖሊስ ጋር በተባበረ መልኩ የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች እንዲቆም ጥሪ

እያደረግን ብሔራዊ ፌዴሽኖችም በሙሉ አቅማችን በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የግንዛቤ

ማሰጨበጫ ስራዎችን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል ተስማምተናል

4/ እኛ የሀገር አቀፍ የሰፖርት ማህበራት የሰፖርት ብሮድካሲቲንግ ተጠቃሚነት መብትን ከዚህ

በፊት ግንቦት 7/2009 ዓ.ም. ባደረግነው ውይይት በተስማማነው መሰረት ብሔራዊ

ፌዴሬሽኖችን በመወከል አስፋላጊውን ህጋዊ ስርዓት በመዘርጋትና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ

እንዲሰራ ለኢትዮጰያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሃላፊነቱን የሰጠን መሆኑን እናረጋግጣለን'

5/ እኛ የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት የሀገራችን የስፖርት ገፅታና ውጤት

ሊያጨልም የሚችለውን አበረታች ቅመሞችን አትሌቶቻችን እንዳይጠቀሙ ተገቢውን ግንዛቤ

ለስፖርት ቤተሰቡ የምንፈጥር መሆኑን እናረጋግጣለን

ጥቅምት 16/2010 ዓ.ም.

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result