የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በ2009 ኦሊምፕአፍሪካ ፉት ቦል ኔት ውድድር አሸናፊ ሆነ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)


የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በ2009 ኦሊምፕአፍሪካ ፉት ቦል ኔት ውድድር ሻምፒዩና ሆነ
የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ደማቅ አቀባበል ተደረገለት


በሱዳን አዘጋጅነት ከሐምሌ 1-2 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው የ2009 የኦሊምፕአፍሪካ የፉት ቦል ኔት ውድድር የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነ፡፡

ቡድኑ አሸናፊ የሆነው ሱዳንን ከወከሉ ሶስት የኦሊምፕአፍሪካ ማዕከል ቡድኖች እና ከሶማሌ ቡድን ጋር ተወዳድሮ ነው፡፡በውድድሩ የኢትዮጵያ ቡድን የሱዳኑን ኦምዱርማንን 2 ለ 1፣በመቀጠል ቡድኑ ከሱዳኑ ሳህፋይ ጋር ተጋጥሞ 0 ለ 0፣ እንዲሁም ከሱዳኑ ኦቤድ ጋር ተጫውቶ የኢትዮጵያ ቡድን 2 ለ1 ረቷል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ቡድን የሶማሌን ቡድን 5 ለ 0 በማሸነፍ በ10 ነጥብ አንደኛ በመውጣት ለሀገሩ ዋናጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

በውድድሩ የሱዳኑ ኦምዱርማን 2ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ የፉት ቦል ኔት ቡድን በአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፣የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና ሌሎች የተቋማቱ አመራሮች በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ

“እናንተ የነገ የሀገር ተስፋዎች ባስመዘገባችሁት አመርቂ ድል እረክተናል”

“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቢሾፍቱ ላይ የሚገኘውን የኦሊምፕአፍሪካ ማዕከል ለማጠናከር አበክሮ ይሰራል፡፡” ብለዋል፡፡

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በበኩላቸው
 
“በዚህ ውጤት ውስጣቸሁ ያለውን እምቅ አቅም ተረድተናል፡፡”

“ተተኪ አትሌቶች ብቻ ሳትሆኑ በስፖርቱ ሴክተር የሀገሪቱ አመራር የመሆን እድሉ አላችሁ..በርቱ፡፡” ብለዋል፡፡
   
የኢትዮጵያ ፉት ቦል ኔት ቡድን በ5 ወንዶች እና በ3 ሴቶች የተዋቀረ ቡድን ነው፡፡

የፉት ቦል ኔት ፕሮግራሙ የኦሊምፒክ ፕሮግራሞች አካል ሲሆን በፕሮግራሙ አማካኝነት ስፖርታዊ ጨዋነትን ማስፈን፣ እርስ በርስ በቡድን ውስጥ እና የተፎካካሪ ቡድን አባላትን ማክበር፣ የቡድን መንፈስ ማጎልበት፣ የአመራር ብቃትን እና ኃላፊነት የመሸከም ክህሎቶችን ለማዳበር የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚተዳደረው የኦሊምፕ አፍሪካ የስፖርት ማዕከል በተለይ የቢሾፍቱ ወጣቶች የእርፍት ጊዜያቸውን ከአልባሌ ቦታ ታቅበው በማዕከሉ በመገልገል አእምሯቸውን እና አካላቸውን በስፖርት እንቅስቃሴ እንዲያዳብሩ ታልሞ የተቋቋመ ማዕከል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፉት ቦል ኔት ቡድን ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው ሁለት ተመሳሳይ ውድድሮች የወርቅ፣ የዋንጫ እና የነሐስ ሽልማት ለሀገሩ ማምጣቱ ይታወሳል፡፡ 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result