የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኦሊምፒክ ቀንን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በሐረር እና ድሬዳዋ ከተሞች አከበረ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኦሊምፒክ ቀንን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በሐረር እና ድሬዳዋ ከተሞች አከበረ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተንቀሳቀስ፣ እውቅ እና ፍጠር በሚል መሪ ቃል በየዓመቱ እ.ኤ አ ሰኔ 23 በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኦሊምፒክ ቀን ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2009ዓ.ም. በተከታታይ ለሁለት ቀናት በሐረር እና ድሬዳዋ ከተሞች አከበረ፡፡

  ዘመናዊ የኢሊምፒክ ቀን የተመሠረተበት እና የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ በዓለማችን እንዲስፋፋና እንዲያድግ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን የኦሊምፒክ ቀን በሁለቱ ከተሞች ሲከበር በሺዎች የሚቋጠሩ የኦሊምፒክ ቤተሰቦች (የህብረተሰብ ክፍሎች) የበዓሉ ታዳሚና ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሠኔ 24 ቀን በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት መዲና በሆነችው ሐረር በዓሉ በተለያዩ የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማለትም በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በእጅ ኳስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ እና በቦክስ ኦሊምፒክ ስፖርቶች ውድድር በማድረግ ተከብሮ ሲውል፣

በሐረር የተከበረው የኦሊምፒክ ቀን ልዩ የሚያደርገው ከ22ኛው የአለም የሐረር ቀን በዓል ጋር ተቀናጅቶ መከበሩ ነው፡፡

 

 

በሁለተኛ ቀን ውሎ ደግሞ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በብስክሌት ስፖርታዊ ኩነቶች የተከበረ ሲሆን፣ ይህ በዓል የኦሊምፒክ እሴቶች የሆኑትን “መከባበር”፣ “ወዳጅነት” እና “የላቀ ውጤታማነት” ማዕከል አድረጎ የተካሄደ ነው፡፡

 

በድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሃር

“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከከተማችን አስተዳደር ጋር በመተባበር ይህን የአለም ኦሊምፒክ ቀን  በዓል በድምቀት በከተማችን በማክበሩ ደስ ብሎናል::”

“ይህ ኩነት የከተማችንን ህብረተሰብ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ በማናቃቃት ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሯል፡፡” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በተካሄዱ የስፖርት ውድድሮች ለተሳተሳፉ ስፖርተኞች  የገንዘብ፣ የስፖርት ቁሳቁሶች እና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

 

በዓሉ የዕድሜ፣ የፆታ፣ የማህበራዊ ሁኔታ፣ የሀይማኖት፣ የቀለም፣ እና የስፖርታዊ ችሎታ (አቅም) ልዩነት ሳይደረግበት የሚከበር ዓለም አቀፍ በዓል ነው፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result