የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካቤኔ ጋር በስፖርት ልማት ዙሪያ መከረ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካቤኔ ጋር በስፖርት ልማት ዙሪያ መከረ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሠኔ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሠ መዲና በሆነችው ጅግጅጋ በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረገ፡፡
ቦርዱ በጉብኝቱ መጀመሪያ በ1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ ተገንብቶ በሶሰት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀውን የጅግጅጋን ኢንተርናሽናል ስታዲየም እና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ትንሷን የጅግጅጋን ስታዲየም ጎብኝቷል፡፡


ቦርዱ በጉብኝቱ ከሌሎች ክልሎች የስታዲየም ጉብኝቶች ያገኘው እና የቀመረውን ልምድና ተሞክሮ ለክልሉ አጋርቷል፡፡
ከስታዲየሞቹ ጉብኝት በኋላ ቦርዱ ከክልሉ ርዕሠ መስተዳደር ከአቶ አቡዱ መሀሙድ ኡመር እና ከባቤኔ አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ መጀመሪያ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለቦርዱ የተደረገውን ደማቅ አቀባበል አመስገነው
“በአቀባበል ሥነስርዓቱ ላይ በተለያዩ ስፖርት አይነቶች የክልሉ ታዳጊ ወጣቶች ያሳዩን ስፖርታዊ ትርኢት የክልሉን ዕምቅ የስፖርት አቅም ያሳየን ነው፡፡”
 “የክልሉ መንግስት የክልሉን ማህበረሰብ በተለይም ወጣቱን በስፖርት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ አስደሳች ነው::”
“ከትልቁ የጅግጅጋ ስታዲየም ግንባታ በተጓዳኝ በትንሽ በጀት በስታዲየሙ ዙሪያ አንድ የስፖርት አካዳሚ ክልሉ ቢሰራ የስፖርት ልማቱ ተሳልጦ ይተሳሰራል፡፡”
“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአቅም ግንባታ አኳያ ክልሉ ሰልጣኞችን አዘጋጅቶ ካሳወቅን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንደየስፖርት አይነቱ አሰልጣኞችን ክልሉ ድረስ በመላክ የተቀናጀ ስልጠና ይሰጣል፡፡
 “ተቀናጅን ከሰሰራር ክልሉ በቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሀገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች እንደሚያፈራ እምነቱ አለን፡፡” ብለዋል፡፡
የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አቶ  አቡዱ መሀሙድ ኡመር በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ  በከፍተኛ ስራ ተነሻሽነት የስራ ጉበኝት ለማደረግ መምጣቱን ካመሰገኑ በኋላ
“ለታዳጊ ወጣቶቻችን በስፖርት ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ምቹ መደላድል ፈጥረን በስፖርቱ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በሚገባ ትኩረት ሠጥተን አልደገፍናቸውም….አልሠራንም::”
 የክልሉ ካቤኔ ቀደም ሲል ለስፖርት የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደነበር የተናገሩት ርዕሠ መስተዳድሩ ካቢኔቸው ለስፖርት ልማት የሚሰጠውን ትኩረት እንደሚያጠናክር ቃል ገልተዋል፡፡
ከአካዳሚ ግንባታ አኳያ የተነሳውንም ጉዳይ ካቢኔቸው እንደሚመክርበት ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ለ6ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ችቦ በቅብብሎሽ ከሚዞርባቸው የክልል ከተሞች መካከል አንዷ ጅግጅጋ መሆኗ ታውቋል፡፡
በክልሉ ባሉ 16 የስፖርት ማህበራት (ፌዴሬሽኖች) ስር ባሉ 16 ስፖርት አይነቶች 889 ሠልጣኞች በ40 አሠልጣኞች እየሠለጠኑ እንደሚገኙ የክልሉ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ  ብለሀሰም  ተናግረዋል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result