“በርካታ አልማዝ አያናዎችን ለመፍጠር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እምቅ አቅሙም እድሉም ያለው ክልል ነው ፡፡”አቶ አሸደሊ ሀሰን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ፕሬዚዳንት

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

“በርካታ አልማዝ አያናዎችን ለመፍጠር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እምቅ አቅሙም እድሉም ያለው ክልል ነው ፡፡”አቶ አሸደሊ ሀሰን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ፕሬዚዳንት

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በስድስተኛ ዙር የስራ ጉብኝቱ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ጋር ሰኔ 5 ቀን 2009 ዓ.ም በመገናኘት ስለ ስፖርት ልማት መከረ፡፡
የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የስራ ጉብኝቱን የኦሶሳን ሁለገብ ስታዲየም በመጎብኘት የጀመረ ሲሆን ቀድሞ ሲል የስራ ጉብኝት ካደረገባቸው ክልሎች ያገኛቸውን ተሞክሮ አጋርቷል፡፡
በመቀጠል የቦርዱ አባላት በክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ጽ/ቤት በመገኘት ከክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አሸዲን ሀሰን እና ከካቤኒ አባላት ጋር የክልሉን ስፖርት ከማልማት አኳያ ምን እየሰራ እንደሆነ እና ወደፊትስ ክልሉ ምን ራዕይ እንደሰነቀ ለመረዳት ውይይት ተደርጎል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል አቶ ተስፋዬ በቀለ የስራ ጉብኝቱን አላማ አስመልክተው ሲገልጹ
“ሀገራችን በምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማነታችን እንዲረጋገጥ ስራችንን ከወዲሁ በበቂ ዝግጅት መጀመር ስላለብን የስራ ጉብኝቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡”


“የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እምቅ አቅም ያላቸው አትሌቶች ያሉበት ክልል ነው፡፡ ለአብነት ያህል በአትሌቲክስ እና በእግር ኳስ ተቀናጅተን ብንሰራ ሀገራችንን የሚያስጠሩ አትሌቶችን ማፍራት እንችላለን፡፡” ብለዋል፡፡
የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር (ፕሬዚዳንት) አቶ አሸደሊ ሀሰን በበኩላቸው የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሥራ ጉብኝት አስመልክተው ሲናገሩ
“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሀገራችንን ስፖርት አሁን ካበት ደረጃ ለማሻሻል እየተከተለ ያለው ስትራቴጂክ አቅጣጫ ውጤታማቱ እና አዋጭነቱ ከወዲሁ ያስታውቃል፡፡”
“የቤንሻንጉል ክልል በርካታ ተሰጥኦ ያላቸው አትሌቶች እንዳሉ በጥናት የተለየ ሀቅ ነው፣ ይሁን እንጂ ለተግባር እንቅስቃሴው ብዙ እርቀት አልሄድንም ፡፡”
“በርካታ አልማዝ አያናዎችን ለመፍጠር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እምቅ አቅሙም እድሉም ያለው ክልል ነው ፡፡”
ስፖርት የሀገራችንን የዕድገት ደረጃ የሚያሳይ አንዱ የልማት ዘርፍ ነው ያሉት አቶ አሸዲን ሀሰን
“የሚመለከተን የስፖርቱ ባለደርሻ አካላት ተናበን እና ተቀናጅተን ከሰራን የሀገራችን የስፖርት ህዳሴ እውን ይሆናል፡፡”ብለዋል፡፡
በምክክሩ ሀገራችን ስለ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች እና ሀገሪቷ በአራት ዓመት ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ስለምትወዳደርባቸው ውድድሮች ዝግጅት እና ተሳትፎ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ አገራችን በስትራቴጂክ ዘመኑ በምታደርጋቸው ወድድሮች ማለትም እ.ኤ.አ 2018 አልጀረስ ላይ ስለሚካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች፣ 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች፣ 2019 ኬፕ ቬርዴ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለሚካሄደው የቢች (Beach) ጨዋታዎች፣ 2018 ቦነስ አይረስ ላይ ስለሚዘጋጀው የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ እና 2020 ላይ ቶክዮ ላይ ስለሚደርገው 32ኛው ኦሊምፒያድ ዝግጅትንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ምክከር አድርገዋል፡፡
የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ በሁለተኛ የሥራ ጉብኝቱ የአሶሳ ዩኒቭርስቲ በመጎብኘት ከዩንቭርስቲው አመራሮች ጋር መክሯል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result