“የጋምቤላ ክልል በርካታ ተሰጥኦ ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ናት ይሁን እንጂ አቅሙን ወደ ጥቅም ለመለወጥ በሚገባው መጠን አልተንቀሳቀስንም ፡፡” አቶ ሰናይ አኳር የጋምቤላ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ርዕሠ መስተዳድር

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

“የጋምቤላ ክልል በርካታ ተሰጥኦ ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ናት ይሁን እንጂ አቅሙን ወደ ጥቅም ለመለወጥ በሚገባው መጠን አልተንቀሳቀስንም ፡፡” አቶ ሰናይ አኳር የጋምቤላ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ርዕሠ መስተዳድር

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በአራተኛ የስራ ጉብኝቱ ከጋምቤላ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ጋር ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም በመገናኘት ስለ ስፖርት ልማት መከረ፡፡
የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በመጀመሪያ ቀን የስራ ጉብኝቱ የጋምቤላን ሁለገብ ስታዲየም በመጎብኘት ቀድሞ ሲል የስራ ጉብኝት ካደረገባቸው ክልሎች ያገኛቸውን ተሞክሮ አጋርቷል፡፡


በመቀጠል የቦርዱ አባላት በጋምቤላ ዩኒቭርስቲ በመገኘት ከዩንቭርሲው ምክትል ፕሬዚዳንት ከዶ/ር ቢየል ቢቾክ እና ከዩኒቭርስቲው የተለያዩ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ዩኒቭርስቲው የክልሉን ስፖርት ከማልማት አኳያ ምን እየሰራ እንደሆነ እና ወደፊትስ ዩኒቭርስቲው ምን ራዕይ እንደሰነቀ በምክትል ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሠፋ የተመራው የስራ አስፈጻሚ ቦርድ
ከክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ከአቶ ሰናይ አኳር እና ከክልሉ ካቤኔ አባላት ጋር በጋምቤላ ግራንድ ሆቴል ስለሀገራችን የስፖርት ልማት በተለይ ስለክልሉ እምቅ የአትሌቶች አቅም መክረዋል፡፡
የኮሚቴው ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሠፋ የስራ ጉብኝቱን አላማ አስመልክተው ሲገልጹ
“ሀገራችን በምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማነታችን እንዲረጋገጥ ስራችንን ከወዲሁ በበቂ ዝግጅት መጀመር ስላለብን የስራ ጉብኝቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡”
“የፌዴራል እና የክልል መንግስታት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የስፖርት ማህበራት እና የሌሎች ባለደርሻ አካላት አቅምን በማቀናጀት የሀገራችን የስፖርት ህዳሴ ለማረጋገጥ እንዲህ ያለው የስራ ግንኙነት ወሳኝ ነው”
“ሀገራችን በያዝነው የአራት አመት ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ በምትሳተፍባቸው ውድድሮች የጋምቤላ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምን አይነት ዝግጀት እየደረገ እንደሆነ ለማየት ነው የመጣነው::”
“በተለይ የጋምቤላ ክልል እምቅ አቅም ያላቸው አትሌቶች ያሉበት ክልል ነው፡፡ ለአብነት ያህል በባስኬት ቦል፣ በቮሊቦል፣ በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ ተቀናጅተን ብንሰራ ሀገራችንን የሚያስጠሩ አትሌቶችን ማፍራት እንችላለን፡፡” ብለዋል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኳር በበኩላቸው የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሥራ ጉብኝት አድንቀው
“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አጀንዳ ሰንቆ ለስፖርታችን እድገት በጋር እንረባረብ ለማለት ወደ ክልላችን ስለመጣ በክልላችን መንግስት እና ህዝብ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡”
“የጋምቤላ ክልል በርካታ ተሰጥኦ ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ናት ይሁን እንጂ አቅሙን ወደ ጥቅም ለመለወጥ በሚገባው መጠን አልተንቀሳቀስንም ፡፡”
“አሁን ግን በዚህ ቀን የማረጋግጥላችሁ የክልላችን የስፖርት ኣቅም ተጨባጭ ፍሬ እንዲያፈራ ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ የቤት ስራችንን ከእናንተ ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን ፡፡”ብለዋል፡፡
በምክክሩ ሀገራችን ስለ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች እና ሀገሪቷ በአራት ዓመት ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ስለምትወዳደርባቸው ውድድሮች ዝግጅት እና ተሳትፎ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ አገራችን በስትራቴጂክ ዘመኑ በምታደርጋቸው ወድድሮች ማለትም እ.ኤ.አ 2018 አልጀረስ ላይ ስለሚካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች፣ 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች፣ 2019 ኬፕ ቬርዴ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለሚካሄደው የቢች (Beach) ጨዋታዎች፣ 2018 ቦነስ አይረስ ላይ ስለሚዘጋጀው የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ እና 2020 ላይ ቶክዮ ላይ ስለሚደርገው 32ኛው ኦሊምፒያድ ዝግጅትንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ምክከር አድርገዋል፡፡
የክልሉ መንግስት የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ ጉብኝት በማድነቅ፣ ከኮሚቴው ጋር በመቀናጀት ለሀገራችን የስፖርት ልማት ዕድገት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ቃል ገብቷል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result