የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጽ/ቤታቸው አነጋገሩ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጽ/ቤታቸው አነጋገሩ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ስፖርታችንን እና የሀገራችን መልካም ገጽታ ግንባታ እንዴት በጋራ እናሳድግ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚኒስቴር መ/ቤቱ መከሩ፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በውይይቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሀገራችን ስፖርት እድገት እየበረከተ ያላውን ድጋፍ አመስግነው የዚህን የጋራ ምክክር መድረክ አላማ ሲገልጹ
“በአራት ዓመት የኦሊምፒክ ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ ሀገራችን ለምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጅትና ተሳታፎ ብሎም ውጤታማነት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጋር ተቀናጅቶ መስረት የማይተካ ሚና ነው ያለው”


“ለቶክዮ 2020 የኦሊምፒክ፣ የወጣቶች ኦሊምፒክ እና ለመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአገራችንን መልካም ገጽታ የሚገነቡ አትሌቶችን በጋራ ማዘጋጀት አለብን::”
“ለዚህ ትልም ስኬት በአገራችን ተቀማጭነታቸውን ካደረጉ ኤምባሲዎች እና አለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር ተቀናጅተን እና ተናበን መንቀሳቀስ ይኖርብናል::” ብለዋል፡፡
ማንኛውም ውጫዊ ግንኙነቶች ስኬት ያለ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እውቅና እና ድጋፍ እውን ሊሆን አይችልም ያሉት ዶ/ር አሸብር
“ስፖርት በባህሪው ከዲፕሎማሲ ስራ ውጪ አይሆንም፡፡ ስፖርት እና ዲፕሎማሲ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው” ብለዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው የዲፕሎማሲን እና የስፖርትን ቁርኝትን እና ታላቅ ፋይዳ ካብራሩ በኋላ
“እንደ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶች ለዲፕሎማሲ ስራችን በጣም ጠቃሚ ናቸው::”
“የስፖርት ጉዳይ በተለይ የኦሊምፒክ ጉዳይ የአገር ገጽታ…የአገር ክብር ጉዳይ ነው፡፡ኦሊምፒክ ሁላችንን በጋራ የሚያስተሳስርን ስፖርታዊ ቋንቋ ነው፡፡”
“የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተልዕኮ ማገዝ ሳይሆን ቋሚ ግንኙነት ፈጥረን አንድ በመሆን አብረናችሁ እንደምንሰራ ቃል እገባላችሀኋለሁ፡፡” ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለሀገራችን ስፖርት እድገት እና ለሀገራችን መልካም ገጽታ ስልጠት በጋራ እንስራ ብሎ ተነሻሽነት በመውሰድ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ድረስ በመምጣት በመምከሩ አድናቆታቸውን እና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት እያንዳንዱ አትሌት እና የስፖርት አመራር እራሱን እና ሀገሩን አክብሮ ለሀገራችን የመልካም ገጽታ ግንባታ እንዲተጋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከህግ ማዕቀፍ እና ከህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲ ምንነት እና ፋይዳ አኳያ ስልጠና እንዲያዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡
ሚኒስትር ዶ/ር ወረቅነህ ገበየሁ የተባለውን ስልጠና ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ ባለው ጉዳይ ላይ በመምክር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ በመደረሱ ደስታቸውን እና ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result