“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ከዚህ በፊት የምናውቀው ለገንዘብ ልመና ሲጎበኘን ነው፡፡” አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ርዕሠ መስተዳድር

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ከዚህ በፊት የምናውቀው ለገንዘብ ልመና ሲጎበኘን ነው፡፡” አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ርዕሠ መስተዳድር

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በሶስተኛ የስራ ጉብኝቱ ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጋር ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም በመገናኘት ስለ ስፖርት ልማት መከረ፡፡
የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በመጀመሪያ ቀን የስራ ጉብኝቱ ከክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ከአቶ ደሴ ዳልኬ እና ከክልሉ ካቤኔ አባላት ጋር በመስተዳድሩ ቢሮ ስለሀገራችን የስፖርት ልማት መክረዋል፡፡
የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የስራ ጉብኝቱን አላማ አስመልክተው ሲገልጹ
“ሀገራችን በምትወዳደርባቸው አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማነታችን እንዲረጋገጥ ስራችንን ከወዲሁ በበቂ ዝግጅት መጀመር ስላለብን የስራ ጉብኝቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡”


“የመንግስት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የስፖርት ማህበራት እና የሌሎች ባለደርሻ አካላት አቅምን በማቀናጀት የሀገራችን የስፖርት እድገት ለማረጋገጥ አላማ አንግቦ የተሰናዳ የስራ ጉብኝት ነው”
“ሀገራችን በያዝነው የአራት አመት ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ በምትሳተፍባቸው ውድድሮች የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምን አይነት ዝግጀት እየደረገ እንደሆነ ለማየት ነው የመጣነው::” ብለዋል፡፡
የክልሉ ርዕሠ መስተዳርድ አቶ ደሴ ዳልኬ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሥራ ጉብኝት አድንቀው
“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ከዚህ በፊት የምናውቀው ለገንዘብ ልመና ሲጎበኘን ነው፡፡”
“ለስፖርቱ እድገት አብረን ተጋግዘን እንስራ ብላችሁ ስለመጣችሁ እጅግ ተደስተናል::”
“ስፖርቱን እንዴት በጋራ ተቀናጀተን እናሳድግ የሚለው አቅጣጫ ጥሩ ጅማሪ ነው፡፡”
“የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከክልሉ ጋር አብሮ ለመስራት ያሳየውን ተነሳሽነት ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል። ብለዋል፡፡
 
በምክክሩ ሀገራችን ስለ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች እና ሀገሪቷ በአራት ዓመት ስትራቴጂክ ዘመን ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ስለምትወዳደርባቸው ውድድሮች ዝግጅት እና ተሳትፎ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ አገራችን በስትራቴጂክ ዘመኑ በምታደርጋቸው ወድድሮች ማለትም እ.ኤ.አ 2018 አልጀረስ ላይ ስለሚካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች፣ 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች፣ 2019 ኬፕ ቬርዴ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለሚካሄደው የቢች (Beach) ጨዋታዎች፣ 2018 ቦነስ አይረስ ላይ ስለሚዘጋጀው የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ እና 2020 ላይ ቶክዮ ላይ ስለሚደርገው 32ኛው ኦሊምፒያድ ዝግጅትንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ምክከር አድርገዋል፡፡
የክልሉ መንግስት የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ ጉብኝት በማድነቅ፣ ከኮሚቴው ጋር በመቀናጀት ለሀገራችን የስፖርት ልማት ዕድገት የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ቃል ገብቷል፡፡
በምክክሩ ላይ የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት ታዳሚዎች ነበሩ፡፡
የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ በሁለተኛ ቀን የሥራ ውሎው ግንቦት 19 ቀን 2009ዓ.ም የሃዋሳን ሁለገብ ስታዲየም እና የሃዋሳ ዩኒቭርስቲን ስታዲየም ጉብኝቷል፡፡
 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result