የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራትን ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ጎበኘ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራትን ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ጎበኘ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሀገራችን በምትወዳደርባቸው ውድድሮች ውጤታማ እንድትሆን “የአሸናፊነት ስልት” ለመንደፍ ከሁሉም ፌዴሬሽኖች ጋር መከረ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና ለጋራ ውጤታማነት የአሸናፊነት ስልት ለመንደፍ የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በተለያዩ አገር፣ አህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጅት እና ተሳትፎ ዙሪያ ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔታል አዲስ ሆቴል ምክክር አደረገ፡፡


ከምክክሩ በፊት በዛው ቀን በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በተባለለት የሥራ ጉበኝት የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ቢሮ በአካል በመገኘት ማህበራቱ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ በተጨባጭ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በጉብኝቱም የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራቱ አደረጃጀት፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በተሟላ ሁኔታ እየሰሩ ሰለመሆናቸው እና ብዛታቸው፣ ማህበራቱ ያሏቸውን የባለሙያዎች ብዛት እና ስብጥር፣ የበጀታቸው ምንጭና መጠን፣ ያሏቸው ውድድሮች እና ስልጠናዎች ብዛት፣ ራስን ከመቻል አኳያ በማከናወን ላይ ስለሚገኙት የማርኬቲንግ ስራዎች፣ መልካም ተሞክሮዎች እና ስለተጋረጡባቸው ችግሮች የሃሳብ ልውውጦች ተደርገዋል፡፡
በከሰዓቱ ፕሮግራም በኢንተርኮንትኔታል አዲስ ሆቴል በተካሄደው ውይይት በመቐለ ከተማ ከሚደረገው 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት እና ከጨዋታው ባሻገር በኩነቱ ስለሚደረጉት ውድድሮች ብሎም ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያ በጋር በቅንጅት መሰራት ስላለባቸው ስራዎች ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመቀጠልም ሀገራችን በአህጉር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ስለምትወዳደርባቸው ውድድሮች፡- 
1.    በ 2018 አልጀርስ ላይ በሚካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች፣
2.    በ 2018 ቦነስ አይረስ ላይ በሚካሄደው 3ኛው የበጋ የወጣቶች ጨዋታዎች፣
3.    በ 2019 ኬፕ ቭርዴ ላይ በሚካሄደው የአፍሪካ ቢች (Beach) ጨዋታዎች፣
4.    በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች እና
5.    በ2020 ቶክዮ ላይ የሚካሄደው የበጋ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች
ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን፣ በውድድሮቹ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result