የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና በባህር ዳር እየሠጠ ነው

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት አስተዳዳር ሥልጠና በባህር ዳር እየሠጠ ነው

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ከግንቦት 5 እስከ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚቆየው ስልጠና ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፌዴሬሽኖች የተውጣጡ 30 የስፖርት ባለሙያዎችና አመራሮች እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ከሠልጣኞች መካከል አስራ ሁለቱ ሴት ስልጣኞች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የአገሪቱን ስፖርት ከማስፋፋት እና ከማሳደግ አኳያ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች መካካል ለዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት አንዱ ነው፡፡ 

በባህር ዳር ከተማ ስልጠናቸውን በመከታታል ላይ የሚገኙት ባለሙያዎችና አመራሮች ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት በየደረጃው ላሉ አካላት በማድረስ ለሀገሪቷ የስፖርት ዕድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ይጠበቃል፡፡ 

 

Total votes : 9
Return to Poll