ፓላኔንፎ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚደንት ሆነው ተቋሙን እንዲመሩ ይሁንታ አገኙ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

ፓላኔንፎ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚደንት ሆነው ተቋሙን እንዲመሩ ይሁንታ አገኙ

የ76 ዓመቱ ፓሌንፎ ለአራተኛ ጊዜ የአኖካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተቋሙን እንዲመሩ በይሁንታ ያለምርጫ ግንቦት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. በጅቡቲ በአኖካ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተመርጠዋል፡፡

አይቮሪኮስታዊው ፓሊንፎ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ውድድር ተፎካካሪ የነበሩት ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ‘ለምርጫው በቁ አይደሉም’ ተብለው ከምርጫው ከታገዱ በኋላ ፓሌንፎ ብቸኛው እጩ ነበሩ፡፡

 

ህጋዊ ባልሆነ እና ሥነ-ምግባር ባልተከተለ መንገድ ካልካባ ለምርጫ ቅስቀሳ የካሜሮንን መንግስት ተጠቅመዋል በሚል ክስ በአኖካ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ውሳኔ መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

ካልካባ አድርገዋል የተባለውን ድርጊት እንዳልፈጸሙ በመናገር ጉዳዩን ለስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት እንዲያቀርቡ ተናግረዋል፡፡

ለዋና ፀሐፊነት (ሴክሬታሪ ጄኔራልነት) የተወዳደሩት የዚምባብዌው ቶማስ ሲቲሆል እና ሱዳናዊው አህመድ አቦ ተወዳድረው ሱዳናዊው 38 በ16 ድምጽ በማሸነፍ የዋና ፀሐፊነት ቦታውን ተረክበዋል፡፡

ናይጄሪያዊው ሀቡ አህመድ ጉሜል የአቃቤንዋይ (ትሬዠረር)፣ አልጄሪያዊው ሙስተፍ ቢራፍ ደቡብ አፍሪካዊውን ጌዶን ሣምን በመርታት የተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታውን ተቆናጠዋል፡፡

ፓሌንፎ ትልቁን የአፍሪካን የስፖርት ተቋም አኖካን እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ ፕሬዚዳንት በመሆን  እየመሩ ይገኛሉ፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result