እጩው የአኖካ ፕሬዚዳንት ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ጅቡቲ በሚካሄደው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (የአኖካ) 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳይታደሙ ታገዱ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

እጩው የአኖካ ፕሬዚዳንት ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ጅቡቲ በሚካሄደው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (የአኖካ) 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳይታደሙ ታገዱ

የአኖካን መንበረ ስልጣንን እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ የተቆናጠጡት አይቮሪኮስታዊው ፓሊንፎ ብቸኛው እጩ የአኖካ ፕሬዚዳንት ሆኑ

ዕጩው ካላካባ ከፕሬዚዳንትነት ዕጩነታቸው አሁን ስራ ላይ ባለው የአኖካ ኤግዚኪዩቲቭ ኮሚቴ ውሳኔ ታግደዋል፡፡

የአኖካ ኤግዚኪዩቲቭ ኮሚቴ ሚያዚያ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈው፡፡

ካልካባ ማብራሪያ እንዲሰጡበት እና የተከሰሱበት ጭብጥ የካሜሮን መንግስት ህጋዊ ባልሆነ አግባብ ለምርጫቸው ዘመቻ ጣልቃ በማይገባበት የአፍሪካ ኦሊምፒክ እንቅስቃሴ ውስጥ  ጣልቃ እንዲገባ እና ለካልካባ የአኖካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ እንዲሰራላቸው በተጨባጭ ተጠቅመዋል የሚል ነው፡፡

ጉዳዩን የመረመረው የአኖካ ኤግዚኪዩቲቭ ኮሚቴ የኦሊምፒክን እና የስፖርት እንቅስቃሴን፣ እንዲሁም የሥነ-ምግባር ህግን የሚጥስ ያልተገባ ድርጊት ነው ብሎታል፡፡

ኤግዚኪዩቲቭ ኮሚቴው ካልካባ ከየትኛውም የአፍሪካ የኦሊምፒክ እና ስፖርት እንቅስቃሴ ስራዎችና ስልጣን በፍጥነት እንዲታደዱ ብሎም ጅቡቲ ላይ ከግንቦት 1 እስከ 3 ቀን 2009 ዓ.ም በሚደረገው የአኖካ 17ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የካሜሮንን ብሔራዊ ኦሊምፒክ እና ስፖርት ኮሚቴ ወክለው መሳተፍ እንደማይችሉ ነግሯቸዋል፡፡ 

የክሱ ጭብጥ ለራሳቸው ለካልካባ፣ ለአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለሁሉም የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች እና ለብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር እንደደረሰ ታውቋል፡፡

ካልካባ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻቸው የሚያደርጉበት ስልት እና ስትራቴጂ አስመልከቶ ያዘጋጁት ምስጢራዊ ሰንድ አፈትልኮ ህጋዊ ባልሆነ አግብብ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡

ካልካባ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ

 “ህጋዊ ባልሆነ አግባብ በተገኘ መረጃ ከአኖካ ጠቅላላ መደበኛ ስብሰባም ብሎም ከምርጫው ልታገድ አይገባም፡፡”

“በተጨማሪም እገዳውን ያስተላለፈው የአኖካ ኤግዚኩዩቲቭ ኮሚቴ በአኖካ ደንብ (ኮንስቲቲውሽን) መሰረት ይህን የመሰል ጉዳይ መርምሮ ውሳኔ የማስተላለፍ ህጋዊ ስልጣን የለውም፡፡” ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያለ ተግባር ተደርጎ አያውቅም፡፡ 

“ይህን ጉዳይ በጥሞና በማጤን የእኔን እጣ ፋንታ መወሰን ያለበት የአኖካ ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ካልካባ ይህን ጉዳይ ለአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥነ-ምግባር ኮሚሽን እንደሚያቀርቡትም አያይዘው ተናግረዋል፡፡ 

የአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ በአኖካ መደበኛ ጠቅላላ መደበኛ ስብሰባ ላይ ታድመዋል፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result