አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ እና ካሜሮናዊው ካልካባ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚዳንት ለመሆን ተፋጠዋል

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

 

አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ እና ካሜሮናዊው ካልካባ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚዳንት ለመሆን ተፋጠዋል

የ76 ዓመቱ አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር የወቅቱ ፕሬዚዳንት ከ 66 ዓመቱ ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል፡፡ 

17ኛው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ከሚቴዎች ማህበር (አኖካ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በጅቡቲ ከግንቦት 1 እስከ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የፕሬዚዳንትነት እና የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫን ዋንኛ አጀንዳው ባደረገው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ይታደማሉ፡፡

የአፍሪካ 54ቱም ሀገሮች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ለፕሬዚዳንትነት ከቀረቡት ሁለት እጩዎች መካከል ለአፍሪካ ኦሊምፒክ እንቅስቃሴ እና ለአህጉሪቷ የስፖርት ዕድገት በጽናት በመቆም ይሰራልናል የሚሉትን መሪያቸውን ይመርጣሉ፡፡

በጠቅላላ መደበኛ ጉባኤው የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትም ምርጫ ይካሄዳል፡፡

የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ጨምሮ ሰባት ለውድድር ክፍት የሆኑ የሥልጣን ቦታዎች ተሰናድተዋል፡፡

ሁለት እጩ ተወዳዳሪዎች ለፕሬዚዳንትነት፣ ሶስት እጩዎች ለተቀዳሚ ፕሬዚዳንትነት፣ ሶስት እጩዎች ለምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚዳንትነት፣ ሶስት እጩዎች ለምክትል ፕሬዚዳንትነት፣ ሁለት እጩዎች ለአራተኛ ደረጃ ምክትል ፕሬዚዳንትነት፣ ሁለት እጩዎች ለሴክሪታሪ ጄኔራልነት፣ እና ሁለት እጩዎች ለአቃቤንዋይ (ትሬዠረርነት) ለመወዳደር ዝግጀታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ለሁሉም ምርጫዎች የቀረቡት የአይቮሪኳስት፣ የካሜሮን፣ የአልጄሪያ፣ የቱኒዚያ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የሶአ ቶሜ፣ የቡርኪና ፋሶ፣ የስዋዚላንድ፣ የጅቡቲ፣ የማዳካስካር፣ የሞሪሺስ፣ የሌሴቶ፣ የኬፕ ቬርዴ፣ የሱዳን፣ የዚምባበዌ፣ የጋምቢያ እና የናይጄሪያ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የስፖርት አመራሮች እጩ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡   

ተመራጩ ፕሬዚዳንት እና የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት የአፍሪካን ከፍተኛውን የስፖርት ተቋም እ.ኤ.አ ከ2017 እስከ 2020 ድረስ ለአራት አመታት ይመራሉ፡

…/

 

የ76 ዓመቱ አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር የወቅቱ ፕሬዚዳንት ከ 66 ዓመቱ ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል፡፡ 

ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2005 እና በ2009 ላይ በተካሄዱ የአኖካ የፕሬዚዳንትንት ምርጫዎች ሁለቱ ባላንጣ (ተፎካካሪ) የስፖርት አመራሮች ተወዳደረው አይቮሪኮስታዊው ፓሌንፎ ሁለት ጊዜ አሸንፈዋል፡፡

(ፓሊንፎ፡- ከ2005 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህብር ፕሬዚዳንት፣ የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የክብር አባል፣ የአይቮሪኳስት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት፣ የአፍሪካ ጁዶ ዩኒየን ፕሬዚዳት እና የአለም ጁዶ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡)

(ካልካባ፡- የአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን እና የካሜሮን ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡)

በጠቅላላ መደበኛ ጉባኤው የምርጫው ሂደት ከመካሄዱ ቀደም ብሎ በመጀመሪያው ቀን በዋንኛነት የሚታዩ ሰባት ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. የአኖካ የ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ተመርምሮ ይፀድቃል፣

2. የሥራ አስፈጻሚ በርዱ እ.ኤ.አ ከ2013-2016 ያለው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ተመርምሮ ይፀድቃል

3. የአቃቤነዋይ (ትሬዠረር) ሪፖረት ተመርምሮ ይፀድቃል

4. የኦዲት ሪፖርት ተመርምሮ ይፀድቃል

5. ከ2017-2020 ለማህበሩ ስራ የተያዘው በጀት ተመርምሮ ይፀድቃል

6. የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ክለሣ

7. የኢዲተሮች ሹመት 

=30=

 

 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result