የቮሊቦል የሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የቮሊቦል የሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

ከሀገሪቱ ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 30 የቮሊቦል አሠልጣኞች ለአምስት ቀናት የተሰጣቸውን የቮሊቦል ሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ስልጠና ተከታትለው አጠናቀቁ፡፡

ሥልጠናው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከኢንተርናሽናል ቮሊቦል ፌደሬሽን እና ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ጋር በጋራ ተዘጋጅቶ የተሰጠ ነው፡፡

 

 

በሥልጠናው የመዝጊያሥነ-ስርዓት ላይ በአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ የተፈረመ ሠርተፍኬት ለሠልጣኞቹ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ በአቶ ታምራት በቀለ ተሰጥቷቸዋል፡፡

 

 

የኮሚቴው ዋና ፀሀፊ አቶ ታምራት በቀለ በመልዕክታቸው

“የወሰዳችሁት የሁለተኛ ደረጃ የአሠልጣኞች ስልጠና በራሱ የመጨረሻ ግብ አይደለም፡፡”

“ያገኛችሁትን እውቀትና ክህሎት በየደረጃው ለሚመለከታቸው የስፖርቱ ተዋንያን ማካፈል እና ማባዛት ትልቁ የቤት ስራችሁ ነው፡፡”

“የዳበረ ልምዳችሁን፣ ዕውቀታችሁን እና ክህሎታችሁን ስራ ላይ በማዋል በዘርፉ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶችን እንደ አትሌቲክሱ የስፖርት ዘርፍ ሁሉ በቮሊቦሉም በማፍራት ሀገራችንን የሚስጠሩ አትሌቶችን መፍጠር ዋንኛው የትኩረት ነጥባችሁ ሊሆን ይገባል፡፡”ብለዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት አፈጸጸማቸው የላቀ ሶስት ሰልጣኞ በኮርሱ ዳይሬክተሮች ተለይተው ለተጨማሪ ስልጠና ውጪ ሀገራት ተልከው ክህሎታቸውን የሚያጎለብቱበት ስልጠና እንደሚመቻችላቸው በስልጠናው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተነግሯል፡፡

 

 

 

 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result