አዲሱ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በስፖርት ልማት ላይ መከረ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)


አዲሱ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በስፖርት ልማት ላይ መከረ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የመጀመሪያውን የስራ ጉብኝት የኮሚቴውን የአመራርነት ኃለፊነት ከተረከበ በኋላ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚያዚያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም አካሄደ፡፡

የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ሚያዚያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም መቀሌ ሲገባ በክልሉ አመራሮች በአሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “የስራ ጉብኝቱ አላማ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ጨዋታዎች የሚተርፈው ትሩፋቶች ፋይዳቸው ከፍተኛ መሆን እንዲችሉ ከወዲሁ የቤት ስራችንን በሚገባ ለመስራት ነው፡፡”“በ6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አቅምና እና ክህሎት ያላቸውን ታዳጊዎች የሚመለመሉበት እና የሚለሙበት ስርዓት አበጅተናል፡፡” ብለዋል፡፡

የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ የመቀሌን ስታዲየም፣ የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ የአትሌቲክስ እና የብስክሌት ክለብ እና የመቀሌ ዩኒቭርስቲን የስፖርት መሰረተ ልማቶች ጎብኝቷል፡፡

ከጉብኝቱ በበርካታ ተሞክሮዎች እና ልምዶች እንደተቀመሩና ልምዶቹም ለሌሎች ክልሎች መተላለፍ እንዳለበት ተነግሯል፡፡

የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በዕለቱ የመጨረሻ ውሎው ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ጋር ክልሉ ባዘጋጀው የራት ግብዣ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ክልሉና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የኢትዮጵያን ስፖርት እድገት ከማጠናከር አኳያ ምን አይነት ስልት በጋራ በመንደፍ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

በምክክሩ ላይ የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት ታዳሚዎች ነበሩ፡፡

 
6ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ችቦ ቅብብሎሽ ፕሮግራም ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር የኦሊምፒክን እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ በስፋት እንዲሳተፍ ከ5ኛው መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ አዘጋጅ ከነበረው እና ችቦ አስረካቢ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በደማቅ ሁኔታ ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውደድሮችን በማዘጋጀት ችቦ በማስረከብ 10 ከተሞችን ችቦው በማቆራረጥ ወደ 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ አዘጋጅ ወደ ሆነው ትግራይ ክልላዊ መንግስት እንደሚደርስ ታውቋል፡፡

የኦሊምፒክ ችቦ በሚያልፍባቸው ከተሞች ሁሉ ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በማካሄድ በርካታ የአካባቢው ወጣቶች በውድድሮቹ እንዲሳተፉ እና ክልላቸውን እንዲወክሉ ብሎም ከተወዳዳሪ ታዳጊዎች መካከል የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ልጆች በባለሙያተኞች በጥንቃቄ ተመርጠው አስፈላጊው ክትትትል እና ድጋፍ ተደርጓላቸው ሀገራችን በምትሳተፍባቸው አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ውድድሮች ተወዳድረው ውጤታማ እንዲሆኑ ዕቅድ ተይዟል፡፡


የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result