በቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ 68 የሚሆኑ አዳዲስ የስፖርት “ኤቭንቶች” እና “ዲስፒሊኖች” እንዲካተቱና እንዲለወጡ ጥያቄዎች ቀረቡበቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ 68 የሚሆኑ አዳዲስ የስፖርት “ኤቭንቶች” እና “ዲስፒሊኖች” እንዲካተቱና እንዲለወጡ ጥያቄዎች ቀረቡ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

በቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ 68 የሚሆኑ አዳዲስ የስፖርት “ኤቭንቶች” እና “ዲስፒሊኖች” እንዲካተቱና እንዲለወጡ ጥያቄዎች ቀረቡ
የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንትና የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አስተባባሪ ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑት ጆን ኮኤትስ በመጪዉ ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከቀደምቶቹ የኦሊምፒክ ስፖርቶች ውስጥ  የሚቀየሩና እንደ አዲስ የሚካተቱ 68 የስፖርት ኩነቶች እና ዲስፒሊኖች እንዲካትቱ ከተለያዩ የአለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ጥያቄ መቅረቡን  በኦሺኒያ ብሄራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡

 


የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለፈዉ አመት በቶኪዮ 2020 ጨዋታዎች  ፕሮግራም ላይ 5 ስፖርቶች በማከል ማለት  ቤዝ ቦል እና ሶፍት ቦል፣ ካራቴ፣ ስኬትቦርዲግ፣ ስፖርት ክላይምቢንግ፣ ሰርፊንግ እንዲካትቱ በማድረግ የኦሊምፒክ ስፖርቶችን ከ28 ወደ 33 ማሳደጉ ይታወሳል፡፡
ጆን ኮኤትስ በቶኪዮ 2020 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዉድድር ላይ ወደ 3010 እና ከዚያም በላይ ሊሆኑ የሚችሉ ኤብንቶች ሊከናወኑ እንደሚችሉ ያላቸዉን ግምት አስታዉቀዋል፡፡
ይህ ለዉጥ የአለም አቀፍ ፌዴሬሽኖችም አሁን ባላቸዉ ፕሮግራም ላይ ተጨማሪ ማሻሻያዎችና ለዉጦች እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል፡፡
ቶኪዮ በጉዳዩ ዙሪያ የፋይናንስ ጫና ያመጣል አያመጣም የሚለዉን በማጥናት ላይ መሆኗ ታውቋል፡፡
እንዲለወጡ አልያም እንደ አዲስ እንዲካተቱ ከተፈለጉት የስፖርት ኩነቶችና ዲስፒሊኖች መካከል የወንዶች ጨዋታ ብቻ የነበሩት የሴቶችም ጭምር እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሁለቱንም ጾታዎች በማቀላቀል ድብልቅ ኩነቶችን (ውድድሮችን) ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
ጥያቄ ከቀረበባቸዉ ዉስጥ ሶስት በሶስት የቅርጫት ካስ  ጨዋታ አንዱ ሲሆን የአለም አቀፉ ጁዶ ማህበር በታህሳስ ወር ላይ ለቶኪዮ 2020 የነጠላ ድብልቅ ቡድን እና በሁለቱም ጾታ በ6 የክብደት ደረጃዎች ማለትም ወንዶች ከ73 ኪ.ግ በታች፣ከ90ኪ.ግ በታች  እና ከ90ኪ.ግ በላይ ሲሆን በሴቶች ከ57ኪ.ግ በታች ፣ከ70ኪ.ግ በታች እና ከ70ኪ.ግ በላይ ዉድድር ጥያቄ ማቅረቡን  ሲናገር የአለም አቀፉ አልሞ መተኮስ ስፖርት ማህበር በበኩሉ በወንዶች ብቻ ሲካሄድ የነበረዉን 3 ኩነቶች ሁሉም በግሩፕ ድብልቅ ዉድድሮች እንዲተካ ጥያቄ ማቅረቡን አስታዉቀዋል፡፡ይህም የህዝቡን ጥያቄና ፍላጎት መሰረት በማድረግ ብቻ ሳይሆን የአይ.ኦ.ሲ ፖሊሲ የሚደነግገዉን የሴቶች እኩል ተጠቃሚነትን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነዉ ተብሎለታል፡፡
ሌላዉ በሴቶች የቦክስ ዉድድር ተጨማሪ ሁለት የክብደት ዉድድሮች  እና እንዲሁም ከሳይክል ዉድድር ጋር በተያያዘም ጥያቄ መቅርቡኝ አስታዉቀዋል፡፡
የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች አስተባበሪ ኮሚሽን የቀረቡትን ጥያቄዎች ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጤን ጉዳዮን አጥንቶ አ.ኤ አ ግንቦት 5/2017 የውሳኔ ሃሳቡን ለአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ 
የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድም ከኮሚሽኑ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር እ.ኤ.አ ሐምሌ ወር ላይ የመጨረሻ ውሳኔውን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result