10ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በ42ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ተመረጡ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

10ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በ42ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ተመረጡ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም.  ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በአስራ ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ መክሮ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ከአጀንዳዎቹ መካከል የ2016 የእቅድ አፈፃፀም፣ የፋይናንስ፣ የኦዲት ሪፖርቶች  ለጉባኤው አባላት ቀርበው  ምክክር ተደርጎባቸው በሙሉ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡
የኮሚቴው የአራት አመት የስትራቴጂክ እቅድም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
ተቋሙን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ ተካሂዶ ተመራጭ አባላቱ ተለይተዋል፡፡


 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ለቀጣዮቹ አራት አመታት ለመምራት ብቸኛ እጩ ሆነው የቀረቡት የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
ዘጠነኛው የኮሚቴው ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ለተኪያቸው አስረኛው የኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብ አስረክበዋል፡፡
በከፍተኛ ክብር የተሰናበቱት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም  "አዲስ የተመረጡት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት የኮሚቴውን የስራ መመሪያዎችና ደንቦች በፍጥነት በመገንዘብ ስራ ላይ ማዋል ይኖርባቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡
ጉባኤው ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ  11 አባላት ያሉት የስራ አስፈፃሚ ቦርድ መርጦል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወክለው ለውድድር የቀረቡት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወክሎ የቀረበው አትሌት ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል ።
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርን በመወከል በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ  አቶ ተስፋዬ በቀለ ፣ ከኢትዮጵያ ፓራ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በመወከል የተከበሩ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ፣ ኦሊምፒያኖችን በመወከል ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኦሊምፒክ ውድድሮች ያልሆኑ ስፖርቶችን በመወከል ከቦውሊንግ አሶሴሽን ወይዘሮ ሔሮዳዊት ዘለቀ ፣ የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ፣  የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ዶክተር ዳዲ ወዳጆ ፣ ከኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን አቶ ዳዊት አስፋው፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን አቶ ኪሮስ ሀብቴን የቦርዱ አባላት ሆነው ተመርጠዋል ።

Total votes : 9
Return to Poll