ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረው የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

ለሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረው የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ


በአስራ ሁለት የቢሾፍቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች መካካል ሲካሄድ የነበረው የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር በስኬት መጋቢት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡
የቤዛ ትምህርት ቤት የስፖርት መምህር አቶ ብስራት ደስታ “ፕሮግራሙ የሰነቀውን ዓላማ በተለይ ስፖርታዊ ጨዋነትን፣ የቡድን ሥራ እና የስር በርስ መከባባር መንፈስን አስፍኖ በስኬት ተጠናቋል፡፡”
“ከእድሜ ተገቢነት ጋር ተያይዞ ተነስተው የነበሩት ውስን አለመግባባቶች በውይይት መፈታታቸው ደስ ፈጥሯልኛል፡፡” ብለዋል፡፡


አስራ አምስት እና ከአስራ አምስት ዕድሜ አመት በታች በሆኑ ታዳጊ ወጣቶች መካካል ሲካሄድ በነበረው ትምህርታዊ ውድድር ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ከ3ሺህ በላይ ታዳሚዎች ተሳትፈውበታል፡፡
የፉት ቦል ኔት ፕሮግራም ሴቶች እና ወንዶች በአንድ ቡድን ውስጥ ተሰባጥረው የሚመሰርቱት ጥንቅር ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በወንዶች ምድብ ወንዶች አራት፣ ሴቶች ሁለት ሆነው በተደራጁበት ውድድር ለምለም ተስፋ ከታን 1ለ0 በመርታት የዋንጫና የኳስ ተሸላሚ በመሆን ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
በሴቶች ምድብ ሴቶች አራት፣ ወንዶች ሁለት በሆኑበት ውድድር ደግሞ ቤዛ ከተኩማ የመጀመሪያ ደረጃ ተገኝተው ቤዛ 3ለ2 በመርታት የዋንጫ እና የኳስ ሽልማት በማግኘት ቀዳሚነቱን ተቀዳጅቷል፡፡ 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result