የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 42ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት ወር ላይ ያካሄዳል

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 42ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት ወር ላይ ያካሄዳል

ኮሚቴውን ለቀጣይ 4 የስትራቴጂክ ዘመን ዓመታት የሚመሩት የሥራ አሰፈጻሚ ቦርድ አባላት ይመረጣሉ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 42ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሪፍት ቫሊ ሆቴል እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሙኒኬሽን ክፍል አስታወቀ፡፡

በ42ኛው የኮሚቴው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤው አባላት በስምንት (8) ጉዳዮች ላይ መክረው ውሳኔ ያሳልፋሉ፡፡

41ኛው (የባለፈው ዓመት) መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ፣2016 የዕቅድ አፈጻጸም፣ የፋይናንስ፣ የኦዲት ሪፖርቶችን፣ የ2017-2020 ረቂቅ ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የ2017 ዓመታዊ ዕቅድ፣ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ ማስፈጸሚያ ረቂቅ መመሪያን መርምሮ ማፅደቅ፣ በመጨረሻም ተቋሙን ለቀጣይ 4 ዓመታት የሚመሩትን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ለ4 ዓመታት ለመምራት ለመወዳደር የሚፈልጉ የስፖርት ማህበራት ዕጩ ተወዳዳሪያቸውን ጠቅላላ ጉባኤው ከመካሄዱ አስራ አምስት ቀናት በፊት መርጠው እንዲያቀርቡ በመመሪያው በተደነገገው መሰረት ፍላጎት ያላቸው ማህበራት እስከ እጩ ማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም 11፡30 ድረስ አስራ አምስት (15) ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል፡፡

 

 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result