”የኦሊምፒክ እና የፓራሊምፒክ ጨዋታዎችን ለአዘጋጅ/ለአስተናጋጅ ከተማ ከአስራ አንድ አመት በፊት እንዲያዘጋጅ መፍቀድ የኦሊምፒክ ቻርተርን ይጥሳል ተባለ”

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

”የኦሊምፒክ እና የፓራሊምፒክ ጨዋታዎችን ለአዘጋጅ/ለአስተናጋጅ ከተማ ከአስራ አንድ አመት በፊት እንዲያዘጋጅ መፍቀድ የኦሊምፒክ ቻርተርን ይጥሳል ተባለ”
“የሚጣስ የኦሊምፒክ ቻርተር የለም…በስፖርቱ ውስጥ ያለውን ተለዋዋጭ ሁኔታ በማጤን የማዘጋጀት እድሉን ከተለመደው ሰባት ዓመት ቀድሞ መስጠት ወቀቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡” የአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማህ ባህ

 የኦሊምፒክ ቻርተር አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ 2 “ልዩ፣ አስገዳጅ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ፣ ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ለሚያስተናግዱ ከተሞች፣ ከኦሊምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት 7 (ሠባት) ዓመታት በፊት የማስተናገድ እድሉ ይሠጣቸዋል፡፡” ይላል:: 
የ2024ን የበጋ ኦሊምፒክ እና የፓራሊምፒክ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት የአሜሪካን -ሎሳንጀለስ፣ የፈረንሳይ-ፓሪስ፣ የጀርመን-ሐምበርግ፣ የጣሊያን-ሮም እና የሀንጋሪ--ቡዳፔስት  በድምሩ አምስት ከተሞች ጨዋታዎቹን ለማዘጋጀት ጥያቄአቸውን አቅርበው እጩነታቸው በአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቀባይን አግኝቶ ወደ መፎካካሪያው ሜዳ ከገቡ በኋላ ከአምስቱ እጩ ከተሞች መካከል በራሳቸው የውስጥ ጉዳይ ምክንያት (ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሣቢያ) እንደቅደም ተከተላቸው የጀርመን-ሐምበርግ፣ የጣሊያን-ሮም፣ የሀንጋሪ ቡዳፔስት ሶስት ከተሞች ከፎክክሩ እራሳቸውን አግለዋል፡፡
ቀሪዎቹ ሁለቱ አያላን የአለማችን ከተሞች ሎሳንጀለስ እና ፓሪስ የ2024ን የበጋ ኦሊምፒክ ለማስተናገድ ብቸኛ ተፎካካሪዎች ሆነው ተፋጠዋል፡፡
9ኛው የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ በአንድ ጊዜ (በአንድ ስብሰባ) የ2024 እና የ2028 የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን አዘጋጅ ከተሞች በመለየትና በመወሰን ሴምቴምበር 13 ቀን 2017 (ከሠባት ወራት በኋላ) ፔሩ-ሊማ ላይ በሚደርገው የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ ላይ ከተሞቹን ይፋ እናድርግ  እያሉ መሞገት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ ፓሪስ እና ሎስአንጀለስ በየፊናቸው የ2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን የማዘጋጀት እድሉ ከተነፈገን ከ11 ዓመታት በኋላ የሚደረገውን የ2028 የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ዳግም እጩ በመሆን የመጫረት ፍላጎቱም ሆነ ፍቃደኝነቱ እንደሌላቸው እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ የለውጥ ስራ መሰራት አለበት ብለው ጽኑ እምነት የያዙት ቶማስ ባህ ጉዳዩን አጥንቶ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ በአራቱ የአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንቶች የሚመራ አጥኚ ቡድን አቋቁመዋል፡፡( የም/ፕሬዚዳንቶቹ ዜግነት እና ስም አውስትራሊያዊው ጆን ኳታስ፣ ቱርካዊው ዩጋር አርጋነር፣ ቻይናዊው ዩ-ዛኩንግ፣ ስፔናዊው ጆን አንቶኒዎ ሳማራንጅ፡፡)
ከስፔናዊው ጆን አንቶኒዎ ሳማራንጅ በስተቀር ቀሪዎቹ ሶሰቱ ምክትል ፕሬዚዳንቶች በአንድ ጊዜ ለሁለት ከተሞች የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን የማስተናገድ ዕድል መስጠትን በይፋ (በአለም የመገናኛ ቡዙሃን አማካይነት) ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቶቹ
“የሚሆን፣ የሚፈጸም ሃሳብ አይደለም::”
“ይደረግ፣ ይሁን እንኳን ቢባል ኦሊምፒክ ቻርተር ውስጥ የተደነገገው አንቀጽ መቀየር አለበት::”
“ከአስራ አንድ አመት በፊት የማስተናገድ ዕድሉን መስጠት ማለት በቻርተሩ መሰረት ሌሎች አዳዲስ ከተሞች እጩ ሆነው እንዳይወዳደሩ ተስፋቸውን ከወዲሁ መቅጨት ነው:: ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ፕሬዚዳን ቶማስ ባህ ለአስተያቱ ምላሽ ሲሰጡ
“የሚጣስ የኦሊምፒክ ቻርተር የለም…በስፖርቱ ውስጥ ያለውን ተለዋዋጭ ሁኔታ በማጤን የማዘጋጀት እድሉን ከተለመደው ሰባት ዓመት ቀድሞ መስጠት ወቀቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡”
“በእኔ የግል አስተያየት ለሁለት ከተሞች በአንድ ጊዜ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን እንዲያዘጋጁ እድሉን መስጠት የኦሊምፒክ ቻርተረን ጥሰትን በፍጹም አያስከትልም፡፡”
“ከተጨባጩ የስፖርት ነባራዊ እድገትና ስጋት ጋር በማገናዘብ ቁርጥ ያለ እና ወቅታዊ ውሳኔ ማስተላለፍ ጊዜው የሚጠይቀው ግልጽ ሀቅ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
አጥኚው ቡድን የበጋን ኦሊምፒክ እና የፓራሊምፒክ ጨዋታዎችን የሚያስተናግዱ ከተሞችን በተመለከተ የኦሊምፒክ ጨዋታ ለማስተናገድ ከተሞች መከተል ስላለባቸው የጨረታ ሂደት፣ የእጩ አቀራረብ ሥነ-ስርዓት እና በተለይ የ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታ ለማስተናገድ በቋመጡት ሁለት ከተሞች ዙሪያ የውሳኔ ሃሳብ ከአራት ወራት በኋላ እ.ኤ.አ ጁላይ 11 እና 12  እንዲያቀርቡ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለታል፡፡
የ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን የማስተናገድ እድሉ ለሎሳንጀለስ የሚሰጥ ከሆነ ከለንደን በመቀጠል የ1932 እና የ1984 የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ያዘጋጀች ከተማ ትሆናለች፡፡
ፓሪስ ደግሞ የ1924 ከበጋ ኦሊምፒክ ጨዋታን ጨምሮ ሁለተኛዋ ጊዜዋ ይሆናል፡፡
   
Total votes : 9
Return to Poll