የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር የቢሾፍቱ ታዳጊ ወጣቶችን የቡድን ስራ ያሳድጋል ተባለ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የፉት ቦል ኔት ትምህርታዊ ውድድር የቢሾፍቱ ታዳጊ ወጣቶችን የቡድን ስራ ያሳድጋል ተባለ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዘጋጅነት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የኮሚቴው ኦሊምፕአፍሪካ የስፖርት ማዕከል የፉት ቦልኔት ትምህርታዊ ውድድር በአስራ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ታዳጊ ተማሪዎች መካከል መጋቢት 9 ቀን 2009ዓ.ም ተጀመረ፡፡

 

 


የፉት ቦል ኔት ፕሮግራሙ የኦሊምፒክ ፕሮግራሞች አካል ሲሆን በፕሮግራሙ አማካኝነት ስፖርታዊ ጨዋነትን ማስፈን፣ እርስ በርስ በቡድን ውስጥ እና የተፎካካሪ ቡድን አባላትን ማክበር፣ የቡድን መንፈስ ማጎልበት፣ የአመራር ብቃትን እና ኃላፊነት የመሸከም ክህሎቶችን ለማዳበር የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው፡፡
የማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ተፈሪ አላምረው ”የፉት ቦልኔት የእግር ኳስ ጨዋታ አላማ አሸናፊነትን የሚያላብሱ ጎሎችን ማስቆጠር አልያም የማሸነፍ ጉዳይ አይደለም…ደስተኛ፣ ጤነኛ፣ አምራች፣ እና ለሀገር እድገት እሴት የሚጨምሩ ታዳጊ ውጤቶችን ማፍራት ነው” ብለዋል፡፡
በፉትቦል ኔቱ ፕሮግራም ከአስራ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ዛሬ የተጀመረው ውድድር በሁለት ዙር መርሃ ግብር  የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓቱን መጋቢት 16 እና 17 ቀን 2009 ዓ.ም በማካሄድ ይጠናቀቃል፡፡
 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚስተዳድረው የኦሊምፕአፍሪካ የስፖርት ማዕከል በተለይ የቢሾፍቱ ወጣቶች የእርፍት ጊዜያቸውን ከአልባሌ ቦታ ታቅበው በማዕከሉ በመገልገል አእምሯቸውን እና አካላቸውን በስፖርት እንቅስቃሴ እንዲያዳብሩ ታልሞ የተቋቋመ ማዕከል ነው፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result