የአትሌት ሶፍያ አሠፋ የለንደን 2012 ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያዋን ከአራት አመት በኋላ አጠለቀች

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የአትሌት ሶፍያ አሠፋ የለንደን 2012 ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያዋን ከአራት አመት በኋላ አጠለቀች

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥር 25 ቀን 2009 ዓ.ም ባዘጋጀው የሜዳሊያ የመስጠት ሥነ-ስርዓት በለንደን 2012 ኦሊምፒክ በሴቶች 3000 መሰናክል ሩጫ ሶሰተኛ ሆና ያጠናቀቀችው አትሌት ሶፍያ አሰፋ ወደ ብር ያደገላትን ሜዳሊያ በደማቅ ስነ-ሥርዓት አጠለቀች፡፡

የዛሬ አራት አመት አትሌት ሶፊያ አሰፋ በተወዳደረችበት በዚሁ ውድድር አንደኛ ወጥታ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀችው ሩሲያዊቷ አትሌት ዮሊያ ዛራፖቫ “ስትሪዮድ ትሪናቦል” የተባለ ንጥረ ነገር ተጠቅማ በመገኘቷ ሳቢያ የአትሌቷ የሜዳሊያ ውጤት በመሰረዙ የደረጃ ሽግሽግ መደረጉ ይታወሳል፡፡

 

የብር ሜዳሊያውን ለአትሌት ሶፍያ አሠፋ ያበረከቱት በአለምአቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ-አስፈጻሚ ቦርድ አባል ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ ሲሆኑ አትሌቷ ሜዳሊያውን እንዳጠለቀች

 

 

 

“ይህ ክብር በወቅቱ ቢሆንልኝ እጅግ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ዛሬም ቢሆን በጣም እረክቻለሁ”

“ከስፖንሰርሺና መሠል ጥቅማጥቅሞች ጋር ተያይዞ ማግኘት ያለብኝን ጥቅማጥቅሞች አጥቻለሁ፡፡”

“ለዚህ ክብር የበኩሉን ከፍተኛ ሚና የተጫወተውን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን አመሠግናለሁ፡፡” ብላለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር በእግዚአብሔር አለበል በበኩላቸው፣

“ንጹህ አትሌቶችን መጠበቅ የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ ተቀዳሚ አጀንዳ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራል፡፡”

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እ.ኤ.አ ከ2017 እስከ 2020 የስትራቴጂክ ዕቅድ ዘመኑ በኢትዮጵያ ስፖርት ላይ ጥቁር ጥላውን ያጠላውን ከኃይል ሠጪና አበረታች መድሃኒቶች ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን የቀውስ አዝማሚያ ለመታገል የእቅዱ አካል ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

በዚህ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግዳነት የታደሙት የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ

 

“በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው አበረታች ቅመሞችን በመጠቀም በተለያዩ ውድድሮች ያለአግባብ ውጤት የማስመዝገብ ችግር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገራችንም ስጋት እየሆነ መጥቷል፡፡”

 

“የዚህ ውጤት መቀየር ለአገራችን ስፖርት በአጠቃላይ እና ለአትሌቲከስ ስፖርት በተለይ ወሣኝ መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡” ብለዋል፡፡

 

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-ዶፒንግ ጽ/ቤት ቦርድ ሠብሳቢ፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዋች ታድመዋል፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result