የኦሊምፒያን የሻምበል አትሌት ምሩጽ ይፍጠር የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኦሊምፒያን የሻምበል አትሌት ምሩጽ ይፍጠር የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ 

የኦሊምፒያኑ የሻምበል አትሌት ምሩጽ ይፍጠር የቀብር ስነ ስርዓት እሁድ ታህሳስ 23 ቀን 2009 ዓ.ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በአገራዊ ክብር ተፈፅሟል።

የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት፤ ታዋቂ አትሌቶች፤ የአትሌቱ ቤተሰቦች እና ወዳጆች በተገኙበት የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተወካዮቻቸው አማካኝነት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሀዘን መግለጫ መልዕክቶች በተቋሙ ኃላፊዎች አማካኝነት አቅርበዋል፡፡

ሀገራችን የዚህን ታላቅ እና ለብዙ አትሌቶች አረአያ የሆነ አትሌት ውለታ መቼውንም እንደማትዘነጋ ተናግረዋል፡፡

አትሌቱ ለኢትዮጵያ የስፖርት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ የገናናው እና የጀግናው አትሌት የህይወት ታሪክ ሲነበብ ተወስቷል፡፡

በሻምበል አትሌት ምሩጽ ይፍጠር የቀብር ስነ ስርዓት ላይ አንጋፋው አትሌት ዋሚ ቢራቱን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የዘጠኙም የሀገራችን ክልሎች እና የከተማ መስተዳድር ተወካዮ እና በርካታ ታዋቂ አትሌቶች ተገኝተዋል። 

 

አትሌት ምሩፅ በ1972 ዓ.ም በሞስኮ በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ተወዳድሮ ድርብ ወርቅ ለሀገሩ ማምጣት የቻለ ታሪካዊ አትሌት ነው።

አትሌቱ ለህክምና ወጪው ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ድጋፍ ተደርጎለታል ነበር።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለመላው የኦሊምፒክ ቤተሰብ፣ ለአትሌቱ ቤተሰቦች፣ የሙያ አጋሮች፣ ወዳጆች እና ጓደኞች መጽናናትን ይመኛል፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result