2ኛው የሀገር አቀፍ የሴቶች ጨዋታ በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

2ኛው የሀገር አቀፍ የሴቶች ጨዋታ በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ሶማሌ 3ኛውን የሀገር አቀፍ የሴቶች ጨዋታ እንዲያዘጋጅ ተመረጠ

ላለፉት ዘጠኝ ተከታታይ ቀናት በሐረሪ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የ2ኛው ሀገር አቀፍ ሴቶች ጨዋታ በሰላም እና በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት ታህሳስ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡

 

በተካሄዱት የኦሊምፒክ ስፖርቶች ውድድር ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና አማራ ከአንድ እሰከ ሶስተኛ ደረጃ ሲይዙ፣ በፓራሊምፒክ ስፖርቶች ደግሞ ኦሮሚያ፣ አማራ እና ደቡብ ከአንድ እሰከ ሶስተኛ ሲወጡ ፣እንዲሁም መስማት በተሳናቸው ጨዋታ ኦሮሚያ፣ አማራ እና አዲስ አበባ ከአንድ እሰከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በመጨረሻም በጨዋታው የመዝጊያ ሥነ-ስርዓት ላይ በጨዋታው አሸናፊ ለሆኑ ክልሎች እና ጨዋታው በሰላም እና በስፖርታዊ ጨዋነት በስኬት እንዲጠናቀቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዋንጫ እና የሰርተፍኬት ሽልማት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡  

በተያያዘ ዜና ታህሳስ 15 ቀን 2009 ዓ.ም በራስ ሆቴል በኦሊምፒዝም መርህ በተቃኘ የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት በተካሄደ ምርጫ የ3ኛው የሀገር አቀፍ የሴቶች ጨዋታን ለማዘጋጀት የተወዳደሩት የኢትዮጵያ-ሶማሌ እና የቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ተፎካክረው የኢትዮጵያ ሶማሌ 7 ለ 3 በሆነ ድምጽ አሸንፎ የአስተናጋጅነት ኃላፊነቱን ተረክቧል፡፡ 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result