6ኛ ቀኑን በያዘው ሁለተኛው የሀገር አቀፍ የሴቶች ጨዋታ ኦሮሚያ የበላይነቱን እንደጨበጠ ነው

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የሴቶች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለሀገራችን ሰፖርት እድገት በሚል መሪ ቃል ከታህሳስ 08 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ጨዋታ የኦሮሚያ ክልል የበላይነቱን እንደጨበጠ ነው፡፡


በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እድል ያላገኙ ሴቶች በስፖርታዊ እንቅስቃሴ በመሳተፍ በሀገር እና በአለምአቀፍ የስፖርት መድረኮች ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ በማለም ሴቶችን ብቻ ማዕከል አድርጎ በተዘጋጀው ጨዋታ በርካታ ተስፋ ያላቸው ተተኪ ሴት አትሌቶችን ማፍራት ተችሏል፡፡


ጨዋታው በኦሊምፒክ፣ በፓራሊምፒክ እና በዲፍሊምፒክ (መስማትበተሳናቸውስፖርት) ጨዋታዎች እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡

በመካሄድ ላይ ባለው የኦሊምፒክ ስፖርቶች ውድድር
በ7 ወርቅ፣ 7 ብርእና 5 ነሐስ ኦሮሚያ፣  በ5 ወርቅ፣ 2 ብርእና 4 ነሐስ ደቡብ፣ በ4 ወርቅ፣ 5 ብርእና 6 ነሐስ አማራ ከአንደ እስከ ሶስት ያሉት ደረጃዎች ሲይዙ፣ አዲስአበባ፣ ትግራይ፣ ድሬዳዋ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ከአራት እስከ አስራ አንድ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸው በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡በተጠናቀቀውየፓራሊምፒክስፖርቶችውድድር

በ15 ወርቅ፣ 9 ብርእና 7 ነሐስ ኦሮሚያ፣  በ9 ወርቅ፣ 9 ብርእና 3 ነሐስ አማራ፣ በ5 ወርቅ፣ 4 ብርእና 11 ነሐስ ደቡብ ከአንደ እስከ ሶስት ያሉት ደረጃዎች በመያዝ ያጠናቀቁ ሲሆን፣ አዲስ አበባ፣ ትግራይ፣ ድሬዳዋ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ከአራት እስከ አስራ አንደኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በመካሄድ ላይ ባለው የዲፍሊምፒክ(መስማትበተሳናቸው) ስፖርቶች ውድድር
በ5ወርቅ፣ 2ብርእና 3ነሐስ ኦሮሚያ፣  በ3ወርቅ፣ 3ብርእና 1 ነሐስ አማራ፣ በ1ወርቅ፣ 3ብርእና 1 ነሐስ አዲስአበባ ከአንደ እስከ ሶስት ያሉት ደረጃዎች ሲይዙ፣ ትግራይ፣ደቡብ፣ድሬዳዋ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ከአራት እስከ አስራ አንድ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸው በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡
በስምንት የስፖርት አይነቶች ማለትም በአትሌቲክስ፣ በእግርኳስ፣ በመረብኳስ፣ በፓራሊምፒክ፣ በዲፍሊምፒክ፣ በቼዝ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ እና በዳርት በመካሄድ ላይ ያለው ጨዋታ ታህሳስ 16 ቀን 2009 ዓ.ም በደማቅ የመዝጊያ ሥነ -ሥርዓትይጠናቀቃል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result