የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

ደረጃ ያውጡለት
(2 ድምፆች)

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ከወራት በፊት የተሾሙት አቶ እርስቱ ይርዳ ህዳር 15 ቀን 2009 ዓ.ም 

የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሜቴን ጎበኙ፡፡

 

በስራ ጉብኝቱ ሚኒስትሩ ኮሚቴው እና ሚኒስቴር መ/ቤቱ እንዴት እጅ ለእጅ ተያይዘው በጋራ ለስፖርቱ እድገት መተባበር እንዳለባቸው ከኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራሮች እና ከኮሚቴው ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር መክረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴ ኤግዚኩዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴን አደረጃጀት፣ የአሠራር ሥርዓት፣ ኮሚቴው እስካሁን በስራ እንቅስቃሴው ለኢትዮጵያ ስፖርት ዘርፍ  እድገት ያደረገውን አስተዋጽኦ፣ በኦሊምፒክ  እና በሌሎች አህጉር እና አለም አቀፍ ጨዋታዎች ዝግጅትና አፈጻፀም ዙሪያ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ሚና ለሚኒስትሩ ገለጻ አድረገዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር ተጋግዞ ለስፖርቱ ማደግ ለመስራት ዝግጅነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡  

በመጨረሻም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሜቴን የሥራ ክፍሎች እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result