የአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ2016 ሴቶቸና ስፖርት ትሮፊ ሽልማት ሰጠ

ደረጃ ያውጡለት
(1 ድምጽ)

የአለም  አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ2016 ሴቶቸና ስፖርት ትሮፊ ሽልማት  ሰጠ

           ኢትዮጵያዊዉ የስፖርት ጋዜጠኛ የአለም ትሮፊ ሽልማትን በመዉሰድ የመጀመሪያዉ ወንድ ሆነ፡፡ ጋዜጠኛ  ዳግም ዝናቡ የአለም  አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ሴቶቸና ስፖርት   የአለም ትሮፊ ከፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ እጅ የተቀበለዉ ሰኞ እለት ምሽት በስዊዘርላንድ ላዉሳኔ በተካሄደ  የሽልማት አሰጣጥ ስነስርአት ላይ ነዉ፡፡ 

 

          ዳግም ለዚህ ሽልማት የበቃዉ እ.ኤ.አ ከ2011 ጀምሮ ልሳን የሴቶቸ ስፖርት ፕሮግራምን በመመስረት ሴቶችና ልጃገረዶች ህልማቸዉን ከግብ እንያደርሱ የሚያበረታታ ስራ በመስራቱ ነዉ፡፡ በዚህ ሬድዮ ፕሮግራም በ አምስት አመታት ዉስጥ 12 580 እንግዶች ሲጋብዝ ከነዚህ ዉስጥ የስፖርት አመራሮችን፤ አሰልጣኞችን ፤ ሴት የስፖርት ባለሞያዎችንና ሴት ስፖርተኞችን በሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ስፖርት ዉስጥ የተሳተፍትን ያካተተ ነበር፡፡ይህ ደግሞ የሴቶችን ስኬትና ያገኙትን  ዉቴት  ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል ከፍትገኛ ሚና ተጫዉቷል፡፡

         ዳግም ይህንን ሽልማት ሲቀበል እንደትናገረዉ   ይህ ሽልማት ለሴቶች ብቻ አይ ደለም ለጾታ እኩልነት ለሚሰሩ ወንዶችም ጭምር  እንጂ፡፡  ይህንን ሽልማት በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ትልቅ እንዳስብም ረድቶኛል ይህ ጅማሬ ነዉ ከሬድዮ ስራ በተጨማሪየቴሌቪዥን  ሾዉ ለመስራት አስያለሁ ይህ ሾዉ በሀገሬ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገሮችም ግንዛቤን ለመፍጠር ያስችላል  ብሏል እንደሚታወቀዉ የሴቶችና ስፖርት ትሮፊ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ በ2000 ነዉ የተካህደዉ፡፡ የአለም  ሴቶችና ስፖርት ትሮፊ የሴቶችና ልጃግርዶችን በሁሉም ደረጃ በስፖርቱ ተሳታፊ  እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ በሀራቸዉ ከዚያም አልፈዉ በአህጉር  ከፍተኛ አስተዋኦ ላደርጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የሚሰጥ ሽልማት ነዉ፡፡ይህ ሽልማት በየአመቱ የሚከናወን ሲሆን አምስት አህጉር አቀፍ እና አንድ አለም አቀፍ በድምሩ ስድስት ነዉ፡፡

በሽልማቱ ስነስርዓት ላይ ለአምስት አህጉራት እና አንድ አለም አቀፍ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

• የአፍሪካ አህጉር አሸናፊ እና ተሸላሚ ወ/ሮ ፊሊሲቴ ሬዌማሪካ ከሩዋንዳ

•የአሜሪካ አህጉር አሸናፊ እና ተሸላሚ ዶ/ር ካርሌ አግሌስባይ ከአሜሪካ

•የኤስያ አህጉር አሸናፊ እና ተሸላሚ ወ/ሮ ማሪያ ኤስታምፓዶር ከፊሊፒንስ

• የኤሮፕ አህጉር አሸናፊ እና ተሸላሚ ወ/ሮ ማጅከን ዚላማርቲን ከዴንማርክ

•የኦሽኒያ አህጉር አሸናፊ እና ተሸላሚ ወ/ሮ ሞያ ዶድ ከአዉስትራሊያ ናቸዉ፡፡

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result