የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ዝግጅት እና ተሳትፎ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና እና ሽልማት ሠጠ

ደረጃ ያውጡለት
(2 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ዝግጅት እና ተሳትፎ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና እና ሽልማት ሠጠ

ሀገራችን  ለተሳተፈችበት የሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ጨዋታ ዝግጅት እና ተሳትፎ  አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥቅምት 28 ቀን 2009 ዓ.ም ዕውቅና እና ሽልማት ሠጠ፡፡

አትሌቶች፣ ባለሙያዎች፣ የበጎ አገልግሎት ፈቃደኞች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት  የሠርተፍኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷላቸዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር በእግዚአብሄር አለበል 

“ይህ የእውቅና ፕሮግራም የሀገራቸውን ስም ላስጠሩ አትሌቶቻችን እና ከአትሌቻችን ጀርባ ደጀን ሆነው ያላሰለሰ ድጋፋቸውን ለሰጡን አካላት ምስጋናችንን የምናቀርብበት ፕሮግራም ነው፡፡”

“ተተኪ ኦሊምፒያን በዚህ የእውቅና እና የሽልማት ሥነ ስርዓት ይነሳሳሉ፡፡”

በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ እና በ5ሺ ሜትር የነሃስ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው ብርቅዬዋ አትሌት አልማዝ አያና የአንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች፡፡

ለዚህ የዕውቅና እና የምስጋና ሥነ-ሥርዓት ሁለት ሚሊዮን ብር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መመደቡ ታውቋል፡፡

ከሀምሌ 29 እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት የሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ጨዋታ በአጠቃላይ በ1 ወርቅ፣ በ2 ብርና በ5 ነሐስ በድምሩ በ8 ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃ፣ ከዓለም 44ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም በሀገራቸው የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ብሎም የሚመሩት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ከሚቴ በርካታ የለውጥ ሥራዎችን እንዲያከናውን ስላስቻሉ “አይ ኦ ሲ ትሮፊ” የተባለ ሽልማት ከአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እንደተበረከተላቸው ታውቋል፡፡

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result