ለ2016 ኦሊምፒክ ወደ ሪዮ ዴ. ጄኔሮ ለሚጓዘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ልዑክ ቡድን ደማቅ አሸኛኘት ተደረገ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ብራዚል ሪዮ ዴጄኒሮ ከተማ ለሚካሄደው 31ኛ ኦሊምፒክ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን ለ13ኛ ጊዜ በመወከል ለሚሳተፉ የልዑካን ቡድን አባላት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በብሔራዊ ቤተመንግስት የአሸኛኘት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በአሸኛኘቱ ፕሮግራሙ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት “እንደቀደምቶቹ አንጋፋ አትሌቶቻችን ሁሉ በእናንተ ወርቃማ ዘመን ለሀገራችሁ እና ለራሳችሁ ታላቅ የሆነ ታሪክ መስራት የምትችሉበት ወቅት ነው፡፡”

“በሀገራችን ሀዝቦች፣ በክልል መንግስታት፣ በከተማ አስተዳደር እና በፌደራል መንግስት ስም የሀገራችንን ሠንደቅ አላማ አደራ የሠጠናችሁ መሆኑን በመገንዝብ እርስ በርሳችሁ በመመረዳዳት እና በመደጋጋፍ ላንጸባራቂ ድል በመብቃት የተሠጣችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ አሣስባለሁ::” ብለዋል፡፡

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው

 “መንግስታችን ለ31ኛው ሪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከምንግዜውም በተሻለ ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ቡድናችን በውጤት እንዲታጀብ ከዝግጅቱ ባለቤቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡”

“በሪዮ ኦሊምፒክ የድል ሠንደቅ አላማችን ደጋግሞ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ እና ብሔራዊ መዝሙራችን ተደጋግሞ እንዲዘመር እንደ ቀደምቶቹ አይበገሬ አትሌቶቻችን የበኩላችሁን ከፍተኛ ጥረት እንድታደርጉ አደራ እላለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

በመቀጠል የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም  

  “ኢትዮጵያውያን ኦሊምፒያን ከወትሮ በተለየ ጠንካር ዝግጅት በማድረጋችሁ ከመቼውም ጊዜ  በላይ ላለምነው ውጤታማነት ብቁ ናችሁ የሚል እምነት ሠንቀናል፡፡”

“እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስም በዚሁ የዝግጅትና የአሸናፊነት መንፈስ እንደምትዘልቁ ከፍተኛ እምነት አለን፡፡” ብለዋል፡፡ የኮሚቴው ፕሬዚዳንት አያይዘውም ለሪዮ 2016 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በስተመጨራሻም የሽኝት ፕሮግራሙ በራት ግብዣ ተጠናቋል፡፡ 

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result