የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ

ደረጃ ያውጡለት
(0 ድምፆች)

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አሰላ ከተማ ለሚገኘው የጥሩነሽ ዲባባ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ'

የ2008 የቤጂንግ ኦሊምፒክ ውጤት መነሻ በማድረግ ለተቋቋመው እና ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት ላይ በሚገኘው የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል ግምታቸው በወቅቱ ገበያ ብር 900,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሺህ) የሚያወጡ የስፖርት ትጥቆችን በማዕከሉ በመገኘት ያስረኩት አቶ ታምራት በቀለ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ናቸው፡፡

 

"ተተኪ ወጣት ስፖርተኞችን ለመርዳት እና ለማገዝ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተግቶ ይሰራል" በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ ታምራት በቀለ ማዕከሉ ተተኪዎችን በማፍራቱ በኩል እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማዕከሉ ለማድረግ  እና በማዕከሉ የሚገኙ የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል'

አያይዘውም በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ከዚህ ማዕከል አገርን የሚወክሉ አትሌቶች እንደሚኖሩ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልፀዋል'

በዚህ የድጋፍ አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ ባለፉት አራት አመታት በአካዳሚው ሲሰለጥኑ የነበሩ እና ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ 56 የእግር ኳስ እና የአትሌቲክስ ሰልጣኞች ተመርቀዋል' ከነዚህ ውስጥ 27 ሴት ስፖርተኞች ይገኙበታል'

በዚህ የምርቃት ስነስርዓት ላይ አቶ ብዙነህ ከቡ የአካዳሚው ዳይሬክተር ባደረጉት ንግግር "አላማችን አትሌቶችን አሰልጥኖ በማብቃት ለክለቦች መመገብ እና የስራ እድል መፍጠር ነው" አካዳሚው ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ መቋቋሙን ገልፀው በነዚህ ጊዜያት በአገር አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ውድድሮች አገራችንን የሚወክሉ ስፖርተኞች ማፍራታቸውን ገልፀዋል'

ለአብነት ያህልም በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ውድድሮች 41 የወንድ እና 46 የሴት በድምሩ 87 አትሌቶች ተሳትፈው የ6 የወርቅ& 5 የብር& 10 የነሐስ እና 19 ዲፕሎማዎች ማስመዝገብ ችለዋል' ከዚህ በተጨማሪ እስከሁን ባለው ሂደት በማዕከሉ 103 አትሌቶችን ለብሔራዊ ቡድን ማስመረጥ እንደቻለ አውስተው ማዕከሉ ለዚህ ከፍተኛ ውጤት እንዲደርስ ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋጽኦ ላደረጉልን ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበው ለተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል'

በስተመጨረሻም በዚህ የምርቃት ስነስርዓት ላይ በመገኘት ለተመራቂዎች እና በትምህርታቸው አመርቂ ውጤት ላመጡ ስፖርተኞች ሰርተፍኬት እና የተለያዩ ሽልማቶችን ያበረከቱት አቶ ታምራት በቀለ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኤክሰኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሲራክ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር እና አቶ ብዙነህ ከቡ ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር ናቸው'

 

የሪዮ 5000ሜ የሴቶችን ዘርፍን ማን ያሸንፋል?

View Result